ምሥጋና (Mesgana) - ሳሙኤል ፡ ቦርሳሞ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሳሙኤል ፡ ቦርሳሞ
(Samuel Borsamo)

Lyrics.jpg


(2)

በጌታ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
(Begieta Hulu Yechalal)

ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ቦርሳሞ ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Borsamo)

 
አዝ፦ ምሥጋና ፡ ተሞልታለች ፡ ነፍሴ (፪x)
አቀርብልሃለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ
ቸርነትህ ፡ ብዙ ፡ ውዱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አጐናጽፈኸኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ

ተረስቻለሁ ፡ ጌታ ፡ ትቶኛል
የተጣልኩኝ ፡ ነኝ ፡ ማን ፡ ያስበኛል
ብዬ ፡ ሳነባ ፡ የራራህልኝ
ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ስላስታወስከኝ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ተሞልታለች ፡ ነፍሴ (፪x)
አቀርብልሃለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ
ቸርነትህ ፡ ብዙ ፡ ውዱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አጐናጽፈኸኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ

ቤት ፡ የሌለው ፡ ሰው ፡ ሆኜ ፡ ከርታታ
ያደላደልከኝ ፡ የእረፍቴ ፡ ጌታ
ለልቤ ፡ ትምክህት ፡ ስለሆንክልኝ
ከፍ ፡ በል ፡ ውዱ ፡ አምላኬ ፡ ስላከበርከኝ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ተሞልታለች ፡ ነፍሴ (፪x)
አቀርብልሃለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ
ቸርነትህ ፡ ብዙ ፡ ውዱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አጐናጽፈኸኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ

ባዶ ፡ ሕይወቴን ፡ በዘይት ፡ ሞልተህ
የነፍሴን ፡ ጥማት ፡ ከእጅህ ፡ አርክተህ
በፍቅርህ ፡ ስበህ ፡ ሰው ፡ ስላረከኝ
ተባረክ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ስለባረከኝ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ተሞልታለች ፡ ነፍሴ (፪x)
አቀርብልሃለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ
ቸርነትህ ፡ ብዙ ፡ ውዱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አጐናጽፈኸኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ

አንተ ፡ ጌታዬ ፡ ሁሌ ፡ በምክርህ
ሰው ፡ እንዳይጠፋ ፡ ነውና ፡ ሃሳብህ
በሕይወት ፡ ቃልህ ፡ ልቤን ፡ አፀናህ
ከፍ ፡ በል ፡ በምድር ፡ ይግነን ፡ ክብርህና ፡ ዝናህ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ተሞልታለች ፡ ነፍሴ (፪x)
አቀርብልሃለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ
ቸርነትህ ፡ ብዙ ፡ ውዱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አጐናጽፈኸኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ