From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ጌታ ፡ አበረታኸኝ ፡ አጠገቤ ፡ ቆሞ
ኢየሱስ ፡ አበረታኸኝ ፡ አጠገቤ ፡ ቆሞ
ፈጥኖ ፡ ደረሰና ፡ ከክፉ ፡ ፊት ፡ ቀድሞ
ነፍሴን ፡ ከሚዋጋ ፡ ከክፉ ፡ ፊት ፡ ቀድሞ
አሰላስላለሁ ፡ የጌታን ፡ በጐነት
በእኔ ፡ ላይ ፡ ያለውን ፡ የአላማውን ፡ ፅናት
ጌታ ፡ አስደንቆኛል ፡ አመስግን ፡ ይለኛል
ምህረቱን ፡ ልዘምር ፡ በእርግጥ ፡ ይገባኛል
ማዳኑን ፡ ልናገር ፡ በእርግጥ ፡ ይገባኛል (፪x)
አዝ፦ ጌታ ፡ አበረታኸኝ ፡ አጠገቤ ፡ ቆሞ
ኢየሱስ ፡ አበረታኸኝ ፡ አጠገቤ ፡ ቆሞ
ፈጥኖ ፡ ደረሰና ፡ ከክፉ ፡ ፊት ፡ ቀድሞ
ነፍሴን ፡ ከሚዋጋ ፡ ከክፉ ፡ ፊት ፡ ቀድሞ
ሲጣሉ ፡ ብቻቸው ፡ ሲታዩ ፡ ግን ፡ በዙ
ከእሳት ፡ የሚታደግ ፡ ማን ፡ ይሆን ፡ ጐበዙ
የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ የኃያላን ፡ ሃያል
በምስሉ ፡ ላይሰግዱ ፡ ከሚጨክኑት ፡ ጋር
ይቆማል ፡ እግዚአብሔር ፡ ስሙን ፡ ሊያስከብር
ጌታ ፡ አስደንቆኛል ፡ አመስግን ፡ ይለኛል
ምህረቱን ፡ ልዘምር ፡ በእርግጥ ፡ ይገባኛል
ማዳኑን ፡ ላወራ ፡ በእርግጥ ፡ ይገባኛል
አዝ፦ ጌታ ፡ አበረታኸኝ ፡ አጠገቤ ፡ ቆሞ
ኢየሱስ ፡ አበረታኸኝ ፡ አጠገቤ ፡ ቆሞ
ፈጥኖ ፡ ደረሰና ፡ ከክፉ ፡ ፊት ፡ ቀድሞ
ነፍሴን ፡ ከሚዋጋ ፡ ከክፉ ፡ ፊት ፡ ቀድሞ
በአርጤክስስ ፡ ዘመን ፡ የሞት ፡ አዋጅ ፡ ወጣ
አይሁድ ፡ እንዲወገድ ፡ ዝክሩ ፡ እንዲታጣ
አዋጁን ፡ ለወጠው ፡ ሞትን ፡ ገለበጠው
ከላይ ፡ ተፈርዶበት ፡ ጽዋውን ፡ ጨለጠው
እግዚአብሔር ፡ ተዋጊ ፡ ስሙም ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
ጌታ ፡ አስደንቆኛል ፡ አመስግን ፡ ይለኛል
ምህረቱን ፡ ልዘምር ፡ በእርግጥ ፡ ይገባኛል
ማዳኑን ፡ ልናገር ፡ በእርግጥ ፡ ይገባኛል (፪x)
አዝ፦ ጌታ ፡ አበረታኸኝ ፡ አጠገቤ ፡ ቆሞ
ኢየሱስ ፡ አበረታኸኝ ፡ አጠገቤ ፡ ቆሞ
ፈጥኖ ፡ ደረሰና ፡ ከክፉ ፡ ፊት ፡ ቀድሞ
ነፍሴን ፡ ከሚዋጋ ፡ ከክፉ ፡ ፊት ፡ ቀድሞ
|