በዛ ፡ ለእኔ (Beza Lenie) - ሳሙኤል ፡ ቦርሳሞ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ቦርሳሞ
(Samuel Borsamo)

Lyrics.jpg


(2)

በጌታ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
(Begieta Hulu Yechalal)

ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ቦርሳሞ ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Borsamo)

 
አዝ፦ በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ምህረትህ ፡ በዛ
በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ቸርነትህ ፡ በዛ
በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ በጐነትህ ፡ በዛ
በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ምህረትህ ፡ በዛ

አገር ፡ መርጬ ፡ ተናግሬአለሁ ፡ በማንነትህ ፡ ስለተመካሁ
ሁሉ ፡ በሁሉ ፡ የሆነ ፡ አባት ፡ አለኝ ፡ ልዩ ፡ የምልበት
ሆነህ ፡ አግኝቼሃለሁ ፡ ከእስትንፋሴ ፡ ቀርበህ
ከምልህም ፡ በላይ ፡ ጌታዬ ፡ ልዩ ፡ ነህ
(፪x)

አዝበዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ምህረትህ ፡ በዛ (፪x)
በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ቸርነትህ ፡ በዛ
በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ቸርነትህ ፡ በዛ

ስሜ ፡ ተፅፎ ፡ በሕይወትህ ፡ መዝገብ
ይህም ፡ ሳያንሰኝ ፡ በምድር ፡ ስታስብ
መጽዓተኝ ፡ ሰው ፡ መሆኔን ፡ ሳውቀው
የጌታዬ ፡ ጣት ፡ ጓዳዬን ፡ ሞላው
በስብከት ፡ ሞኝነት ፡ የወደድኩት ፡ ጌታ
በፍቅሩ ፡ ማረከኝ ፡ መጥቶ ፡ በዝግታ
በስብከት ፡ ሞኝነት ፡ የመረጥኩት ፡ ጌታ
የእራሱ ፡ አደረገኝ ፡ መጥቶ ፡ በዝግታ

አዝበዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ፍቅርህ ፡ በዛ (፪x)
በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ምህረትህ ፡ በዛ
በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ በጐነትህ ፡ በዛ

ያለ ፡ ኢየሱስ ፡ ራቁቱን ፡ ቆሞ
ፈውስ ፡ ይላል ፡ ቃል ፡ ገጣጥሞ
ወግ ፡ ማዕረግ ፡ ረስቶ ፡ ፍፁም ፡ እርካታ
በኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ሰላም ፡ አፎይታ
የተገረማችሁ ፡ በሚያስገርም ፡ ጌታ
ደስታችሁን ፡ ግለጹ ፡ በሆታ ፡ በደስታ
(፪x)
የተደነቃችሁ ፡ በሚያስደንቅ ፡ ጌታ
ደስታችሁን ፡ ግለጹ ፡ በሆታ ፡ በዕልልታ
(፪x)

አዝበዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ቸርነትህ ፡ በዛ (፪x)
በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ በጐነትህ ፡ በዛ
በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ቸርነትህ ፡ በዛ

ሃሌሉያ ፡ አሜን