በማለዳ (Bemaleda) - ሳሙኤል ፡ ቦርሳሞ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ቦርሳሞ
(Samuel Borsamo)

Lyrics.jpg

(2)

በጌታ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል
(Begieta Hulu Yechalal)

ቁጥር (Track):

(1)

ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ቦርሳሞ ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Borsamo)

አዝ፦ በማለዳም ፡ ምሥጋና ፡ በቀትርም ፡ ምሥጋና ፡ በሌሊትም ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ይገባሃልና (፪x)

ከየቀኑ ፡ ክፋት ፡ ስምህ ፡ ታድጐን
በቁሳቁስ ፡ ብዛት??? ፡ ልጅህ??? ፡ ተጥሎ
ከሚርመሰመሰው ፡ ከአመጽ ፡ ጦር
ተዋግተህ ፡ አሸንፈን ፡ ኢየሱስ ፡ አለን ፡ ከአንተ ፡ ጋር

አዝ፦ በማለዳም ፡ ምሥጋና ፡ በቀትርም ፡ ምሥጋና ፡ በሌሊትም ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ይገባሃልና (፪x)

ሃዘንን ፡ በደስታ ፡ ጥማት ፡ በርካታ
ርሃብን ፡ በጥጋብ ፡ ጭንቀት ፡ በእፎይታ
ሁሉንም ፡ በጊዜው ፡ ውብ ፡ አድርገህ ፡ የሰራህ
የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ኢየሱስ ፡ ይባረክ ፡ ስምህ

አዝ፦ በማለዳም ፡ ምሥጋና ፡ በቀትርም ፡ ምሥጋና ፡ በሌሊትም ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ይገባሃልና (፪x)

ትንሿ ፡ አንደበቴ ፡ ምን ፡ ብላ ፡ ታውራ
አሳልፈኸኛል ፡ ጽኑውን ፡ መከራ
ውለታህ ፡ ያለበት ፡ ቆሞ ፡ ያመስግንህ
ሌላ ፡ ምን ፡ ልበልህ ፡ አንተ ፡ ክብሩ ፡ ነህ

አዝ፦ በማለዳም ፡ ምሥጋና ፡ በቀትርም ፡ ምሥጋና ፡ በሌሊትም ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ይገባሃልና (፪x)

ስለ ፡ ታላቅ ፡ ስራህ ፡ የምለው ፡ አለኝ
በምክርም ፡ በድንቅ ፡ በሳቅ ፡ ሞላኸኝ
ከዘለዓለም ፡ እስከ ፡ ዘለዓለም ፡ ድረስ
ዙፋንህ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ ውዴ ፡ አንተ ፡ ተወደስ

አዝ፦ በማለዳም ፡ ምሥጋና ፡ በቀትርም ፡ ምሥጋና ፡ በሌሊትም ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ይገባሃልና (፪x)