ፀጋውን ፡ ገለጠና (Tsegawen Geletena) - ሳሙኤል ፡ አበበ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ አበበ
(Samuel Abebe)


(1)

የመንገዴ ፡ መብራት
(Yemengedie Mebrat)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ አበበ ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Abebe)

አዝ፦ ኧረ ፡ የትኛው ፡ ነው ፡ የኔ ፡ መልካም ፡ ሥራ
ለመዳኔ ፡ ምክንያት ፡ ሆኖ ፡ የሚጠራ
የራሴ ፡ ጥረት ፡ ግረት ፡ ያለኝ ፡ አቅም ፡ ጉልበት
ከቶ ፡ ኣላዳነኝም ፡ ከዘላለም ፡ ውድቀት

ሕሊናዬን ፡ ሲወቅሰኝ ፡ እየደገመ ፡ ሲከሰኝ
ዓለም ፡ መሞትን ፡ ስትሰብከኝ
ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ሕይወት ፡ ሆነልኝ
ተስፋ ፡ መቁረጥን ፡ ስትነግረኝ
ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ተስፋ ፡ ሆነልኝ (፪x)

ከዓለም ፡ ጋር ፡ ተጣብቄ
በኃጢያት ፡ ገመድ ፡ ታንቄ
ፀጋውን ፡ ገለጠና ፡ አስካደኝ ፡ ወረሰኝና
መንፈሱን ፡ አፈሰሰና ፡ ለያየኝ ፡ የራሱ ፡ አረገኝና (፪x)

አዝ፦ ኧረ ፡ የትኛው ፡ ነው ፡ የኔ ፡ መልካም ፡ ሥራ
ለመዳኔ ፡ ምክንያት ፡ ሆኖ ፡ የሚጠራ
የራሴ ፡ ጥረት ፡ ግረት ፡ ያለኝ ፡ አቅም ፡ ጉልበት
ከቶ ፡ ኣላዳነኝም ፡ ከዘላለም ፡ ውድቀት (፪x)