የእኔ ፡ ዓለሜ (Yene Aleme) - ሳምራዊት ፡ ሲዛር

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳምራዊት ፡ ሲዛር
(Samrawit Sizar)

Lyrics.jpg


(2)

የእኔ ፡ ዓለሜ
(Yene Aleme)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፩ (2019)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 6:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳምራዊት ፡ ሲዛር ፡ አልበሞች
(Albums by Samrawit Sizar)

የእኔ ፡ ደስታ ፡ ኢየሱስ አሃ ።

የእኔ ፡ ዓለሜ ፡ የአንተ ፡ ክብር ፡ ነው /2/
የእኔ ፡ ዓለሜ ፡ የአንተ ፡ መንፈስ ፡ ነው /2/
የእኔ ፡ ዓለሜ ፡ የአንተ ፡ ክብር ፡ ነው /2/
የእኔ ፡ ዓለሜ ፡ የአንተ ፡ መንፈስ ፡ ነው /2/

የሰው ፡ ልጅ ፡ ምኞቱ ፡ ከፍታ ፡ ስኬቱ
በመደረግ ፡ ያልፋል ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ ከንቱ
ሕይወት ፡ ተገለጠ ፡ ለእኔም ፡ በርቶልኛል
ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ ያሻኛል

ከአንተ ፡ ሌላ ፡ አያምረኝም /2/
ከአንተ ፡ ውጪ ፡ አያምረኝም /2/

ናፍቆቴ ፡ ነህ ፡ ምኞቴ ፡ ነህ
ጉጉቴ ፡ ነህ ፡ ሕይወቴ ፡ ነህ

የለም ፡ እንዳንተ ፡ ምወደው
የለም ፡ እንዳንተ ፡ ምናፍቀው
የለም ፡ እንዳንተ ፡ ምወደው
የለም ፡ እንዳንተ ፡ ምናፍቀው

በመንፈስ ፡ የሆነ ፡ ሰላም ፡ የሞላው
ሃዘን ፡ የሌለበት ፡ የአንተ ፡ ዓለም ፡ ነው
ዳግመኛ ፡ ብፈጠር ፡ እድሉን ፡ ባገኝ
ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የምታጓጓኝ

ከአንተ ፡ ሌላ ፡ አያምረኝም /2/
ከአንተ ፡ ውጪ ፡ አያምረኝም /2/

የእኔ ፡ ዓለሜ ፡ የአንተ ፡ ክብር ፡ ነው /2/
የእኔ ፡ ዓለሜ ፡ የአንተ ፡ መንፈስ ፡ ነው /2/
የእኔ ፡ ዓለሜ ፡ የአንተ ፡ ክብር ፡ ነው /2/
የእኔ ፡ ዓለሜ ፡ የአንተ ፡ መንፈስ ፡ ነው /2/

አንተ ፡ ነህ ፡ ሰላም ፡ አንተ ፡ ነህ
(የዚህ ፡ ቤት ፡ ሰላም ፡ የዚህ ፡ በቤት ፡ ክብር)
ኢየሱስ ፡ (ኦሆሆ ፡ ሃሌሉያ)