ትውስ ድቅን (Tiwus Diken) - ሳምራዊት ሲዛር

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሳምራዊት ሲዛር
(Samrawit Sizar)

Lyrics.jpg


(2)

Yene Aleme
(Yene Aleme)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፪ (2019)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳምራዊት ሲዛር ፡ አልበሞች
(Albums by Samrawit Sizar)

ትውስ ድቅን ይልብኛል አይኔ ላይ
እየሱሴ መስቀሉ ላይ
የተወጋው ጎኑ ደሙ የፈሰሰው
እኔን ከሃጥያቴ ሊያጥበኝ ነው
የቆሰለም ጀርባው የተገረፈው
እኔን ከእግዚአብሔር ጋር ሊያስታርቀኝ ነው

እንዴት ነው የምትወደኝ/3
ምህረትህ ሰው አረገኝ

ደምህ ሲፈስልኝ በቀራንዮ ላይ
እርግማኔን ስትወስድ ስትሞት መስቀል ላይ
ያን ሁሉ አበሳ ለኔ ነው ለኔ ነው
ማንም አላስገደደህ ፍቅር ይዞህ ነው/2

ፍቅርህ ያንተን ፍቅር እየሱስ
የትም አላየሁት ማንም ላይ አላየሁት

ልዩ ነው ፍቅርህ/4

ባነበብኩት ብቻ አይደለም
በሰማሁት ብቻ አይደለም
ምህረትህ እየተከተለኝ
ስቀድቅ እርሱ አይደለም ወይ የሚያነሳኝ
ስደክም የሚያቆመኝ

አንተ መልካም አንተ መልካም ነህ
ኧረ አንተ መልካም አንተ መልካም ነህ

መልካም ነህ መልካም ነህ
አንተ መልካም ነህ

ክበርልኝ አንተ የኔ ጌታ
ክበርልኝ አንተ የኔ ወዳጅ/4

ትውስ ድቅን ይልብኛል አይኔ ላይ
እየሱሴ መስቀሉ ላይ
የተወጋው ጎኑ ደሙ የፈሰሰው
እኔን ከሃጥያቴ ሊያጥበኝ ነው
የቆሰለም ጀርባው የተገረፈው
እኔን ከእግዚአብሔር ጋር ሊያስታርቀኝ ነው

እንዴት ነው የምትወደኝ/3
ምህረትህ ሰው አረገኝ