ቃልህ (Qaleh) - ሳምራዊት ሲዛር

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሳምራዊት ሲዛር
(Samrawit Sizar)

Lyrics.jpg


(2)

Yene Aleme
(Yene Aleme)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፪ (2019)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳምራዊት ሲዛር ፡ አልበሞች
(Albums by Samrawit Sizar)

አፀናኸ ልቤን ምንም እንዳይሆን
በፈተና ጎርፍ እንዳይወሰድ

ንፋሱ ነፍሶ ዝናቡም ዘንቦ
ህይወቴን ቤቴን አላፈረሰውም
ያምላኬ ቃሉ ልቦና ሰቶኝ
ቤቴን ባለት ላይ አይደል ወይ ያሰራኝ

የተዘራውን ቃል አልበሉትም ወፎች
የሰማሁትን ቃል አልያዘውም እሾህ
በመንፈስ ታርሶ ነው የገባው ልቤ ውስጥ
በውሃ ዳር እንዳለ ዘፍ ፍሬው አይቋረጥ
በወንዝ ዳር እንዳለ ዘፍ ፍሬው አይቋረጥ

ቃልህ ይይዘኛል/4

ደክሜ እንዳልጠፋ ቃልህ ይይዘኛል/2
ደክሜ እንዳልጠፋ ቃልህ ይይዘኛል/2

በእጄ ቃል አለ በእጄ ላይ/3
አሸናፊ አረገኝ የበላይ

መልካም እድል የማይወሰድ
ከእግርስ በታች ጌታ መሆን
መልካም እድል የማይወሰድ
ከእግሮችህ ስር ሆና ቃልህን መማር

ይሁንልኝ ይሁንልኝ
የኔ አባት አንተው ምራኝ አስተምረኝ/2
ኦ መንፈስ ቅዱስ አንተ አውራኝ አስተምረኝ/2
ይሁንልኝ ይሁንልኝ
የኔ አባት አንተው ምራኝ/2
መንፈስ ቅዱስ አንተ አውራኝ አነጋግረኝ አስተምረኝ