ለዚህ ነው (Lezi New) - ሳምራዊት ሲዛር

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሳምራዊት ሲዛር
(Samrawit Sizar)

Lyrics.jpg


(2)

Yene Aleme
(Yene Aleme)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፪ (2019)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳምራዊት ሲዛር ፡ አልበሞች
(Albums by Samrawit Sizar)

ለዚ ነው መዘመር ያልተውኩት
ለዚ ነው አምልኮም ያልተውኩት
ለዚ ነው ተመስገን የምለው
እንዳንተ ስላላገኘው ነው

ለዚ ነው አምልኮ ያልተውኩት
ለዚ ነው መውደዴን ያልተውኩት
ለዚ ነው ተመስገን የምለው
እንዳንተ ስላላገኘው ነው

ተመችተኸኛል ከማንም በላይ
ውስጤን ያሳረፍካት አንተ አይደለህ ወይ
ተመችተኸኛል ከማንም በላይ
ነፍሴን ያሳረፍካት አንተ አይደለህ ወይ

ይሄ ሁሉ ሰላም ይሄ ሁሉ ደስታ
በዚ አለም አይደለም ነው እኮ በጌታዬ
በብርና በወርቅ የማይገዛውን
ሰላሙን ሰቶኛል በቃ ላምልከው
በብርና በወርቅ የማይገዛውን
ደስታውን ሰቶኛል እኔም ላምልከው

ገና አመልክሃለው/8

አይጨልምብህም አይነጋም ጠብቆ
አንተው ብርሃን ነህ ትገርማለህ እኮ

ሁሉም ነገር ባንተ እጅ ላይ ስላለ
አልፎ ያመልክሃል ባንተ የታመነ
ሁሉም ነገር ባንተ እጅ ላይ ስላለ
አልፎ ያመልክሃል አንተን የታመነ

አመክሃለው የኔ ወዳጅ አመልክሃለው/2

ገና አመልክሃለው/8

በዘመኔ የማልተወው የማላቆመው
እግዚአብሔርን የኔን ወዳጅ ማገልገሌን ነው
እግዚአብሔርን የኔን አባት ማገልገሌን ነው

በዘመኔ የማልተወው የማላቆመው
እግዚአብሔርን የኔን አባት ማገልገሌን ነው
እግዚአብሔርን የኔን ተስፋ ማገልገሌን ነው

ይሄ ሁሉ ሰላም ይሄ ሁሉ ደስታ
በዚ አለም አይደለም ነው እኮ በጌታ
በብርና በወርቅ የማይገዛውን
ሰላሙን ሰቶኛል በቃ ላምልከው
በብርና በወርቅ ያልተደገፈው
ደስታውን ሰቶኛል እኔም ላምልከው