እረኛዬ ነው (Eregnaye New) - ሳምራዊት ሲዛር

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሳምራዊት ሲዛር
(Samrawit Sizar)

Lyrics.jpg


(2)

Yene Aleme
(Yene Aleme)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፪ (2019)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳምራዊት ሲዛር ፡ አልበሞች
(Albums by Samrawit Sizar)

እግዚአብሔር እረኛዬ ነው
ሚያሳጣኝ የለም የማጣው የለም/2
እግዚአብሔር ፀጥታዬ ነው
ሚያውከኝ የለም/3

የማመልከው አምላክ የተደገፍኩት
ጠበቀኝ እንዳልጠፋ እኔ እንዳልሞት
በእጆቹ መዳፍ ላይ ስለቀረፀኝ
አልጠፋም የሚራራ አባት አለኝ

የማያስከፍል ቅጥር ሆኖኛል መተማመኛ
ማስፈራራቱ አያገኘኝም የዛ ቀማኛ
የሚጠብቀኝ የኔ አባት
አይሰለቸውም ቀንም ለሊት
የሚጠብቀኝ የኔ እረኛ
ቀኑን ጠብቆ ማታ ማይተኛ

በቀኜ ነህና እኔ አልደነግጥም
ሁልግዜ ስላማህ አልታወክም
ከመከራ ስጋት ልቤ እርፍ ብሏል
ህይወቴ በእጅህ ላይ ነው ምን ያስፈራኛል

የማያስከፍል ቅጥር ሆኖኛል መተማመኛ
ማስፈራራቱ አያገኘኝም የዛ ቀማኛ
የሚጠብቀኝ የኔ አባት
አይሰለቸውም ቀንም ለሊት
የሚጠብቀኝ የኔ እረኛ
ቀኑን ጠብቆ ማታ ማይተኛ

እኔ የምኖረው አንተን ታምኜ ነው/2
በህይወት የምኖረው ቃልህን ታምኜ ነው/2

እግዚአብሔር እረኛዬ ነው
ሚያሳጣኝ የለም የማጣው የለም/2
እግዚአብሔር ፀጥታዬ ነው
ሚያውከኝ የለም/3