በየማለዳው (Beyemaledaw) - ሳምራዊት ሲዛር

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሳምራዊት ሲዛር
(Samrawit Sizar)

Lyrics.jpg


(2)

Yene Aleme
(Yene Aleme)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፪ (2019)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳምራዊት ሲዛር ፡ አልበሞች
(Albums by Samrawit Sizar)

በየማለዳው ያንተ ውለታ
ይከተለኝ በጠላት እንዳልረታ
አይዞሽ ስትለኝ ስታስበኝ
ከአፌ መዝሙር እንዳይጠፋ አደረከኝ

ምን ልበል ምን ላድርግ ወዶኝ ነው ያለልክ/2

ዛሬ ዛሬስ ይገርመኛል
ሰው መሆኔ ይደንወኛል
ባለፍኩበት ጎዳናዬ
መከናወኔ ነው ጌታዬ

አሃሃ ከፍ በል ኦሆሆ ከፍ በል/2
አሃሃ ከፍ በል

ዛሬን ባንተ ካለፍኩ ነገን ምን እሆናለው
ክንድህ አስተማማኝ ተደግፌዋለው
ዛሬን ባንተ ካለፍኩ ነገን ምን እሆናለው
ቃልህ አስተማማኝ ተደግፌዋለው

ካላጣኸ ቦታ ካላጣኸው ልብ
ኧረ እንዴት ወደድከኝ ገረመኝ ሳስብ

ማነው የወደደኝ ጠጋ ያረገኝ
ከመሞት አውጥቶ ፍቅር ያሳየኝ

ጌታ ነው/3 ጌታ

አንዴ በቻ አይደለም ብዙ ጊዜ ነው ጉልበት የሆንከኝ
እምነቴ ሲላላ ከጎኔ ቀመህ ያበረታኸኝ
መቼም መቼም መቼም ቢሆን አልረሳውም ያንተን ፍቅር
ሰው ያረክኝ ያወጣኸኝ ከጨለማው ከሞት ገደል/2

በየማለዳው ያንተ ውለታ
ይከተለኝ በጠላት እንዳልረታ
አይዞሽ ስትለኝ ስታስበኝ
ከአፌ መዝሙር እንዳይጠፋ አደረከኝ

ምን ልበል ምን ላድርግ ወዶኝ ነው ያለልክ/2

የኔማ ነገር የኔ ጉዳይ ተፈፀመልኝ ጎልጎታ ላይ
የኔማ ነገር የኔስ ጉዳይ ተፈፀመልኝ ጎልጎታ ላይ
መቼም መቼም መቼም ቢሆን አልረሳውም ያንተን ፍቅር
ሰው ያረክኝ ያወጣኸኝ ከጨለማው ከሞት ገደል/2