From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ምን ፡ አጣሁኝ ፡ ብለህ ፡ ወጣህ ፡ ከአባትህ ፡ ቤት
ሄድክ ፡ ርቀህ ፡ ሰላም ፡ ደስታ ፡ ወደ ፡ ሌለበት
አባትህ ፡ አሁንም ፡ እቤት ፡ ካሉት ፡ ይልቅ
ያሰባል ፡ ሰለአንተ ፡ ይናፍቃል ፡ ይጠብቃል
ሚመለሰው ፡ ልጄ ፡ መቼ ፡ ነው ፡ እያለ
የጠፋው ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ አንተ ፡ አይደለህ ፡ ወይ
መመለስህን ፡ ሁልጊዜ ፡ ይናፍቃል ፡ ሊያይ
መመለስህን ፡ ሁልጊዜ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይናፍቃል ፡ ሊያይ
ና ፡ ተመለስ ፡ ሁሉን ፡ ትተህ ፡ እርሳውና
የአባትህ ፡ እጅ ፡ ዛሬም ፡ ለአንተ ፡ ነው ፡ እንደተዘረጋ
በትር ፡ ይዞ ፡ እኮ ፡ አይደለም ፡ ሚጠብቅህ
ታውቀዋለህ ፡ አንዳይለወጥ ፡ እግዚአብሔር ፡ እንደሚወድህ
"ወንድሜ ፡ ብዙዎች ፡ በቤቱ ፡ ቢኖሩም
ስለጠፋኀው ፡ስለአንተ ፡ ዘወትር ፡ ያስባል
ወደ ፡ ቤቱ ፡ የምትመለስበትን ፡ ሰዓት ፡ ይጠባበቃል
የክብር ፡ ልብስ ፡ ሊያለብስህ
የምህረት ፡ ደጆቹ ፡ ሁልጊዜ ፡ ለአንተ ፡ ክፍት ፡ ናቸው
በአባትህ ፡ ቤት ፡ መኖር ፡ ለአንተ ፡ ይሻልሃል
ወስነህ ፡ እንዲ ፡ በል"
ኢሄው ፡ መጣሁ ፡ ወደ ፡ ቤት
ተመልሻለሁ ፡ እንድትምረኝ
በክርስቶስ ፡ አስቀድሜ ፡ ተይቃለሁ
እኔም ፡ ልጅህ ፡ ናፍቄያለሁ
አባቴ ፡ አንተን ፡ ይሄው ፡ ልጅህ
መጥቻለው ፡ ብትቀበለኝ
ወድሃለሁ (፪x) ፡ እግዚአብሔር ፡ ወስኛለሁ
አዲስ ፡ ጉዦ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ልጀምር ፡ ወስኛለሁ
አዲስ ፡ ጉዦ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ልጀምር
|