From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
(ትዝ ፡ ይለኛል)
አዝ:- ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ቀኑ (፪x)
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በደምብ
ከሞት ፡ የተረፍኩበት
አስቤ ፡ አላደረኩት ፡ ቀጠሮም ፡ አልነበረኝ
በድንገት ፡ በአጋጣሚ ፡ በስፍራው ፡ ተገኘሁኝ (ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ቀኑ)
ወደቤተ ፡ መቅደሱ ፡ ወደውስጠኛው ፡ ስገባ
ተሰማኝ ፡ የእግዚአብሔር ፡ የአምላኬ ፡ ህልውና (ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ቀኑ)
አዝ:- ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ቀኑ (፪x)
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በደምብ
ከሞት ፡ የተረፍኩበት
ሰሰማን ፡ ህልውናው ፡ በደስታ ፡ ውስጤ ፡ ሲሞላ
ከዐይኖቼ ፡ ሲፈሱ ፡ የደስታ ፡ የሃሴት ፡ እምባ (ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ቀኑ)
እጆቼን ፡ ዌርሱ ፡ አንስቼ ፡ በቃ ፡ የአንተ ፡ ነኝ ፡ ስለው
ለዘለዓለም ፡ ወስኜ ፡ ሕይወቴን ፡ ስሰጠው (ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ቀኑ)
አዝ:- ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ቀኑ (፪x)
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በደምብ
ከሞት ፡ የተረፍኩበት
አንደበቴ ፡ ለክብርህ ፡ መከፈት ፡ ሲጀምር
ሰዎችም ፡ ሲደነቁ ፡ በአደረክልኝ ፡ ነገረ (ግርም ፡ ይለኝ ፡ ጀመር)
ይቅርታን ፡ ከአንተ ፡ ጠይቄ ፡ ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ
እንደገና ፡ በቤትህ ፡ አጽንተህ ፡ ስትተክለኝ (እጅግ ፡ ተደሰትኩኝ)
አዝ:- ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ቀኑ (፪x)
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በደምብ
ከሞት ፡ የተረፍኩበት
ማንነቴ ፡ ተቀይሮ ፡ አዲስ ፡ ፍጥረት ፡ ሆንኩኝ
የኋላዬን ፡ ረስቼ ፡ የፊቴን ፡ እያየሁኝ (ጉዞዬን ፡ ጀመርኩኝ)
ድል ፡ በድል ፡ እየጨመረ ፡ ነገሬ ፡ እያማረልኝ
የሚያውቀኝ ፡ ሰው ፡ በሙሉ ፡ ሲገረም ፡ ሲደነቅብኝ (ጌታዬን ፡ አከበርኩኝ)
አዝ:- ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ቀኑ (፪x)
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በደምብ
ከሞት ፡ የተረፍኩበት
|