From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ:- ትልቅ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ትልቅ ፡ ትልቅ (፬x)
አይችልም ፡ ምንም ፡ ማንም ፡ ከአንተ ፡ ሊልቅ (፬x)
ጉልበተኛ ፡ ነው ፡ ከተባለ ፡ ምንም ፡ ነገር
ተለካክቶ ፡ ነው ፡ ተወዳድሮ ፡ ከሌላው ፡ ጋር
አንተ ፡ ምድርን ፡ ሰማያትን ፡ እንኳን ፡ ስጸራ
የተጠቀምከው ፡ ቃልህን ፡ ነው ፡ ከአፍህ ፡ የወጣ
ቃልህ ፡ ያልተፈጠረውን ፡ መፍጠር ፡ ከቻለ
እንዴት ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ ነገርህ ፡ ልበል ፡ ልናገር ፡ ለአንተ
አዝ:- ትልቅ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ትልቅ ፡ ትልቅ (፬x)
አይችልም ፡ ምንም ፡ ማንም ፡ ከአንተ ፡ ሊልቅ (፬x)
የአንተ ፡ የሆኑት ፡ ልጆችህ ፡ ከአንተ ፡ የወጡት
ቃልህን ፡ በውስጥ ፡ መንፈሳቸው ፡ ስላስቀመጡት
እነርሱ ፡ ሳይቀር ፡ የአንተን ፡ ቃል ፡ ሲናገሩት
ስጋን ፡ ተላብሰው ፡ ሰራዊት ፡ ሆኗል ፡ ደረቅ ፡ አጥንት
ዝናብ ፡ እንዳይወርድ ፡ ተከልክሎ ፡ ፀሐይ ፡ ቆማለች
አይደለም ፡ አንተ ፡ ልጆችህ ፡ ናቸው ፡ ሃይለኞች
አዝ:- ትልቅ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ትልቅ ፡ ትልቅ (፬x)
አይችልም ፡ ምንም ፡ ማንም ፡ ከአንተ ፡ ሊልቅ (፬x)
ቀላል ፡ ነው ፡ በአንተ ፡ እይታ ፡ ሳየው
ይሆናል ፡ ቃል ፡ ስትወጣ ፡ ወዲያው
ባለ ፡ ስልጣን ፡ ነህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ባለስልጣን
ግር ፡ ግር ፡ የለም ፡ ስትናገር ፡ ሁሉ ፡ ይሰማል
ይሆንልሃል ፡ እንደአፍህ ፡ አንተ ፡ እንዳልከው
ስላመንኩብህ ፡ አንተን ፡ ነው ፡ የማመልከው
አዝ:- ትልቅ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ትልቅ ፡ ትልቅ (፬x)
አይችልም ፡ ምንም ፡ ማንም ፡ ከአንተ ፡ ሊልቅ (፬x)
|