ቃልኪዳን ፡ ገባሁኝ (Qalkidan Gebahugn) - ሩት ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሩት ፡ ታደሰ
(Ruth Tadesse)

Ruth Tadesse 1.jpg


(1)

ሰማያዊ ፡ ዜግነት
(Heavenian Citizen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሩት ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Ruth Tadesse)

 
እኔ ፡ የእርሱን ፡ ላውጋው ፡ የፈጠረኝን
እርሱም ፡ ስለእኔ ፡ ሁሉን ፡ ሊያውቅልኝ
ስምምነት ፡ አደረኩ ፡ ቃልኪዳን ፡ ገባሁኝ
እግዚአብሔርን ፡ ብቻ ፡ ላውቀው ፡ እርሱም ፡ ለእኔ ፡ ሊያውቅልኝ

አዝ:- ቃልኪዳን ፡ ገባሁኝ (፪x)
እኔ ፡ የእርሱን ፡ ብቻ ፡ ላውቀው
እርሱም ፡ ለእኔ ፡ ሊያውቅልኝ (፪x)

የሰማሁት ፡ ጥበብ ፡ የተቀበልኩት
በፈጠረኝ ፡ ጌታ ፡ ሲታይ ፡ ሞኘነት
እስከዛሬ ፡ ለእኔ ፡ አውቄ ፡ የአደኩበት
ገባኝ ፡ መልካምነት ፡ ምንም ፡ እንደሌለበት
ስለዚህ ፡ ነው ፡ እኔን ፡ በቃ??? ፡ ወሰንኩት
አዳኜ ፡ አድርጌ ፡ የተቀበልኩት

አዝ:- ቃልኪዳን ፡ ገባሁኝ (፪x)
እኔ ፡ የእርሱን ፡ ብቻ ፡ ላውቀው
እርሱም ፡ ለእኔ ፡ ሊያውቅልኝ (፪x)

ልክ ፡ እንደእረኛ ፡ የሚሄድ ፡ ፊት ፡ ፊቴ
ከጐኔ ፡ እንዳላጣው ፡ አብሮኝ ፡ ሁልጊዜ
ሳጠፋ ፡ ስሳሳት ፡ ሳለሁ ፡ በድካሜ
ዞር ፡ ስል ፡ ምህረቱ ፡ የለ ፡ ከኋላዬ
እንደእርሱ ፡ ያለ ፡ አምላክ ፡ ከየት ፡ አገኛለሁ
ምህረቱ ፡ አስደናቂ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነው

አዝ:- ቃልኪዳን ፡ ገባሁኝ (፪x)
እኔ ፡ የእርሱን ፡ ብቻ ፡ ላውቀው
እርሱም ፡ ለእኔ ፡ ሊያውቅልኝ (፪x)

ለእናንተስ ፡ ዕውቀት ፡ ማነው ፡ የነገራቹህ
ስለእናንተ ፡ ሕይወት ፡ ጠልቆ ፡ ሚያውቅላቹህ
ጠጋ ፡ በሉት ፡ እርሱን ፡ ሩህሩህ ፡ ባሕሪውን
የሰዎች ፡ ጥያቄ ፡ ችግር ፡ ሚገባው
ከእስትንፋስ ፡ የሚቀርብ ፡ ፍቅርን ፡ የተሞላ
ማይሰለች ፡ ወዳጅ ፡ ነው ፡ እመኑበት ፡ ብቻ

አዝ:- ቃልኪዳን ፡ አድርጉ ፡ ከእርሱ (፪x)
እስከ ፡ መቼም ፡ አይጥላቹህ
እርሱ ፡ ይሁን ፡ እረኛቹህ (፪x)