አዋቂ ፡ ነው (Awaqi Neh) - ሩት ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሩት ፡ ታደሰ
(Ruth Tadesse)

Ruth Tadesse 1.jpg


(1)

ሰማያዊ ፡ ዜግነት
(Heavenian Citizen)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሩት ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Ruth Tadesse)

 
አዝ:- አዋቂ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ አዋቂ ፡ ነው (፭x)
አዋቂ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው

ጽንሷ ፡ መዘግየቱ ፡ ያሳዝናል
ሃና ፡ ባትረዳ ፡ ባይገባት
ጌታ ፡ በእርሷ ፡ ያየው ፡ ትልቅ ፡ ሰው
አስቦ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ለእራሱ ፡ ሊለየው

ረስታ ፡ ሃና ፡ የእግዚአብሔርን ፡ አዋቂነት
ካሰበችው ፡ በላይ ፡ ሲሆን ፡ ድንገት
የእርሱ ፡ ስራው ፡ ለጊዜ ፡ አስደናቂ
አለች ፡ እርሷም ፡ ግርም ፡ ሲላት ፡ኧረ ፡ አዋቂ

አዝ:- አዋቂ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ አዋቂ ፡ ነው (፭x)
አዋቂ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው

ኤልያብ ፡ ነው ፡ በሰው ፡ ሚዛን ፡ የበለጠው
በነቢዩ ፡ ዐይን ፡ እንኳን ፡ ቀድሞ ፡ የገባው
ፊትን ፡ አልፎ ፡ ሚመረምር ፡ የልብን
እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ መረጠው ፡ ዳዊትን

የጓዳውን ፡ ሰው ፡ ሳያየው ፡ ስለሚያውቀው
እረኛውን ፡ በስልጣን ፡ ላይ ፡ አስቀመጠው
ጠብቆ ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ ስለሚያውቀው
ሲመርጥ ፡ እርሱ ፡ አይሳሳትም ፡ አዋቂ ፡ ነው

አዝ:- አዋቂ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ አዋቂ ፡ ነው (፭x)
አዋቂ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው

የትኛውን ፡ ነገሬን ፡ ነው ፡ ምደብቀው
እግዚአብሔር ፡ ሁሉን ፡ ያያል ፡ አዋቂ ፡ ነው
በሰዎች ፡ መመረጥ ፡ ቀርቶብኝ
ይሁንልኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያየልኝ

ጅማሬውን ፡ ፍጽሜውን ፡ ስለሚያውቀው
ይሻለእኛል ፡ ምንም ፡ ቢሆን ፡ እርሱ ፡ ያለው
መልካም ፡ ስለሆነ ፡ የሚያስበው
የመረጠው ፡ እርሱ ፡ ለእኔ ፡ ምርጫዬ ፡ ነው

አዝ:- አዋቂ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ አዋቂ ፡ ነው (፭x)
አዋቂ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው