ዘላቂ ፡ ዋስትና (Zelaqi Wastena) - ሮማን ፡ ሳሙኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሮማን ፡ ሳሙኤል
(Roman Samuel)

Roman Samuel 3.jpg


(3)

ነገሩ ፡ ተገለበጠ
(Negeru Tegelebete)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሮማን ፡ ሳሙኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Roman Samuel)

በኃጥያት ፡ ባርነት ፡ ከታሰርንበት
የሞትን ፡ ሽታ ፡ ካጣጣምንበት
ወደ ፡ ፅድቅ ፡ አደባባይ ፡ ጠርተኸን
በሕይወት ፡ መዓዛ ፡ ይኸው ፡ ታወድን

የጥሪህ ፡ ተስፋ ፡ አስደናቂ ፡ ነው
የርስትህም ፡ ክብር ፡ እኩያ ፡ የለው
ስለሰጠኸን ፡ የመዳን ፡ ዕውቀት
ተመካን ፡ በኃይልህ ፡ ታላቅነት

አማኑኤል (፮x)
አሜን ፡ ይብዛልህ ፡ ምሥጋና (፫x)
አስተማማኝ ፡ ነህ ፡ ዘላቂ ፡ ዋስትና

ከድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ውስጥ ፡ ወጥተና
ከሞት ፡ ጥላም ፡ ሃገር ፡ አምልጠናል
በሚደነቅ ፡ ብርሃን ፡ ልታኖረን
አዲስ ፡ ምዕራፍ ፡ ተከፈተልን

በቃል ፡ ኪዳንህ ፡ እየደገፍከን
በሸለቆ ፡ ህግህን ፡ አስተማርከን
እስከ ፡ ዘንድሮ ፡ በአንተ ፡ ዘልቀናል
ከእጆችህ ፡ መዳፍ ፡ ማን ፡ ያወጣናል

አማኑኤል (፮x)
አሜን ፡ ይብዛልህ ፡ ምሥጋና (፫x)
አስተማማኝ ፡ ነህ ፡ ዘላቂ ፡ ዋስትና

ማግኘት ፡ ማጣት ፡ መብዛት ፡ መጉደልን
መክበር ፡ መዋረድ ፡ መራብ ፡ መጥገብን
መነቀፍ ፡ መሞገሥም ፡ አይተናል
ጉልበት ፡ ሆነኸን ፡ ሁሉን ፡ ችለናል

ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ነህ ፡ ማን ፡ ይከሰናል
አፀደከን ፡ ማን ፡ ይኮንነናል
ከአሸናፊዎች ፡ በአንተ ፡ እንበልጣለን
የለም ፡ ከፍቅርህ ፡ የሚነጥለን

እንዲህ ፡ መተናል ፡ ያለፈውን ፡ ዘመን
ስለ ፡ ነገውስ ፡ ምን ፡ አስጨነቀን
ኃያልነትህ ፡ እጅግ ፡ አስመካን
ኦ ፡ የእኛ ፡ ጌታ ፡ ተመሥገንልን

ዝማሬ ፡ አለን ፡ እስከዛሬ
ዕልልታ ፡ ዘላቂ ፡ አለኝታ
ጭብጨባ ፡ ሽብሸባ
የዘለዓለም ፡ አምባ
እኛስ ፡ በጐነት ፡ የለንም