ዛሬም ፡ ይኸውልህ (Zariem Yeheweleh) - ሮማን ፡ ሳሙኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሮማን ፡ ሳሙኤል
(Roman Samuel)

Roman Samuel 3.jpg


(3)

ነገሩ ፡ ተገለበጠ
(Negeru Tegelebete)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሮማን ፡ ሳሙኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Roman Samuel)

በዘመናት ፡ . (1) . ፡ ግን ፡ አላረጀህም
የዓመታት ፡ እርዝማኔ ፡ አላታከተህም
ትናንት ፡ ዛሬ ፡ ለዘለዓለም ፡ አንተ ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ
ኃያል ፡ ንጉሥ ፡ እግዚአብሔር ፡ የምትገርም ፡ አምላክ ፡ ነህ (፭x)
እንኳን ፡ አመለኩህ ፡ አንኳን ፡ ሰገድኩልህ
ገናም ፡ አልበቃኝም ፡ ዛሬም ፡ ይኸውልህ

አዲስ ፡ ምሥጋና (፬x) ፡ ዛሬም ፡ ይኸውልህ (፭x)
ማልጄ ፡ ልዘምር ፡ ደግሞም ፡ ቀን ፡ በቀትር
ምሽትም ፡ ጨምራለሁ ፡ ይኼም ፡ ሲያንስህ ፡ ነው (፪x)
ምሥጋናዬ ፡ አይነስህ ፡ ይደራረብ ፡ በመቅደስህ (፪x)

ብዙ ፡ አማልክት ፡ ወድቀዋል ፡ ለጥቂት ፡ ተደንቀው(?)
መታሰቢያ ፡ እንኳን ፡ አጥተዋል ፡ ዘመን ፡ አልፎባቸው
አንተ ፡ ግን ፡ እንዳማረብህ ፡ በዙፋንህ ፡ ላይ ፡ ነህ
ኃያል ፡ ንጉሥ ፡ እግዚአብሔር ፡ እጅግ ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነህ (፭x)
እንኳን ፡ አደነኩህ ፡ እንኳን ፡ ሰገድኩልህ

ገናም ፡ አልበቃኝም ፡ ዛሬም ፡ ይኸውልህ
አዲስ ፡ ምሥጋና (፭x) ፡ ዛሬም ፡ ይኸውልህ (፭x)
በታላላቅ ፡ ጉባኤ ፡ በጓዳም ፡ ለብቻዬ
መስዋዕቴ ፡ ያርግልህ ፡ ጣፋጭ ፡ መዓዛ ፡ ይሁንልህ (፪x)
አምልኮዬ ፡ አደነልህ ፡ ይደራረብ ፡ በመቅደስህ (፪x)

ፍቅር ፡ ምህረት ፡ ቸርነትህ ፡ ማልዶ ፡ ማልዶ ፡ አዲስ ፡ ነው
አሮጌ ፡ ታሪክ ፡ የለህም ፡ ብርታትህም ፡ ያው ፡ ነው
የቅድስናህም ፡ ክብር ፡ እያደር ፡ ይደምቃል
ኃያል ፡ ንጉሥ ፡ እግዚአብሔር ፡ ዝናህ ፡ ምድርን ፡ ሞልቷል (፭x)
እንኳን ፡ አወደስኩህ ፡ እንኳን ፡ ዘመርኩልህ
ገናም ፡ አልበቃኝም ፡ ዛሬም ፡ ይኸውልህ

አዲስ ፡ ምሥጋና (፭x) ፡ ዛሬም ፡ ይኸውልህ (፬x)
ካየሁት ፡ ከሰማሁት ፡ ለነፍሴ ፡ የቀረላት
በአንተ ፡ መደነቅ ፡ ነው ፡ ዋናም ፡ ትርፍም ፡ የሆነላት (፪x)

ምሥጋናዬ ፡ አይነስህ
ዝማሬ ፡ አይነስህ
አምልኮዬ ፡ አይነስህ
አክብሮት ፡ አይነስህ
ይደራረብ ፡ በመቅደስህ