የከበበኝ (Yekebebegn) - ሮማን ፡ ሳሙኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሮማን ፡ ሳሙኤል
(Roman Samuel)

Roman Samuel 3.jpg


(3)

ነገሩ ፡ ተገለበጠ
(Negeru Tegelebete)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሮማን ፡ ሳሙኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Roman Samuel)

የከበበኝ ፡ የደገፈኝ ፡ አሃሃ
የቀደመኝ ፡ የተከተለኝ (፪x)
አምላኬ ፡ ነው ፡ የሚያኖረኝ (፮x)
እግዚአብሔር ፡ ነው

የጓደኛዬ ፡ ነገር ፡ የአየሩ ፡ ሁኔታ
የዘመን ፡ ወጣ ፡ ውረድ ፡ የጠላት ፡ ድንፋታ
አይደለም ፡ ሚዛኔ ፡ ነገን ፡ የምለካበት
ቃልኪዳን ፡ ይዣለው ፡ እምነቴን ፡ የምጥልበት

እርሱ ፡ አይለወጥም ፡ አምላኬ ፡ አይለወጥም
እግዚአብሔር ፡ አይለወጥም
ስለዚህ ፡ እኔ ፡ አልጠፋም (፫x)

የከበበኝ ፡ የደገፈኝ ፡ አሃሃ
የቀደመኝ ፡ የተከተለኝ (፪x)
አምላኬ ፡ ነው ፡ የሚያኖረኝ (፮x)
እግዚአብሔር ፡ ነው

የጨባጭ ፡ መረጃ ፡ ቢያቀብለኝ ፡ ኖሮዬ
እኔም ፡ መረጃ ፡ አለኝ ፡ ቃል ፡ ሰጥቶኛል ፡ ጌታዬ
እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ አቤነዘር ፡ ብያለሁ
ትናንት ፡ የረዳኝን ፡ ነገም ፡ እታመነዋለሁ

እርሱ ፡ አይለወጥም ፡ አምላኬ ፡ አይለወጥም
እግዚአብሔር ፡ አይለወጥም
ስለዚህ ፡ እኔ ፡ አልጠፋም (፫x)

የክብር ፡ አምላክ ፡ የክብር
አብሮኝ ፡ ሆነና ፡ እግዚአብሔር
ያስጨነቀኝ ፡ አዋረዳቸው
እንደ ፡ መንገድ ፡ ጭቃ ፡ ረገጣቸው
የክበር ፡ ንጉሥ ፡ የክብር
ቀድሞኝ ፡ ወጣና ፡ እግዚአብሔር
ጠላቶቼን ፡ ሁሉ ፡ አወካቸው
እንደ ፡ ትብያ ፡ እንደ ፡ እብቅ ፡ በተናቸው

እርሱ ፡ አይለወጥም ፡ አምላኬ ፡ አይለወጥም
እግዚአብሔር ፡ አይለወጥም
ስለዚህ ፡ እኔ ፡ አልጠፋም (፫x)

መብልና ፡ መጠጥ ፡ የድንኳኔ ፡ ውበት
መቀበሪያ ፡ ሥፍራ ፡ የአሟሟቴም ፡ ዓይነት
አይደለም ፡ ጭንቀቴ ፡ እኔን ፡ የሚያሳስበኝ
ከዚህ ፡ የሚሻገር ፡ የደመቀ ፡ ተስፋ ፡ አለኝ

እርሱ ፡ አይለወጥም ፡ አምላኬ ፡ አይለወጥም
እግዚአብሔር ፡ አይለወጥም
ስለዚህ ፡ እኔ ፡ አልጠፋም (፫x)

የከበበኝ ፡ የደገፈኝ ፡ አሃሃ
የቀደመኝ ፡ የተከተለኝ (፪x)
አምላኬ ፡ ነው ፡ የሚያኖረኝ (፮x)
እግዚአብሔር ፡ ነው