የእግዚአብሔር ፡ ቃል (YeEgziabhier Qal) - ሮማን ፡ ሳሙኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሮማን ፡ ሳሙኤል
(Roman Samuel)

Roman Samuel 3.jpg


(3)

ነገሩ ፡ ተገለበጠ
(Negeru Tegelebete)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሮማን ፡ ሳሙኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Roman Samuel)

ሃብቴ ፡ ነው ፡ ሃብቴ ፡ ሃኪሜም ፡ መድኃኒቴ
ከሞት ፡ ጉዞ ፡ መለሰኝ ፡ በሕይወት ፡ ጐዳና ፡ መራኝ
ዝናብ ፡ ምድርን ፡ እንዲያርስ ፡ ውስጤን ፡ አረስርሶታል
ለአምላኬ ፡ ክብር ፡ እንድኖር ፡ ለፅድቅ ፡ አነቃቅቶኛል

የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ይባረክ (፬x)

. (1) . ፡ አስደነቀኝ ፡ ፈተሸኝ ፡ መረመረኝ
ከክፉ ፡ . (2) . ፡ መክሮ ፡ በልቤ ፡ ተሰውሮ
ማስተዋሌን ፡ አስፈትቶ ፡ በትዕዛዙ ፡ ሮጣለሁ
የእለት ፡ መመሪያዬ ፡ አስተዳዳሪዬም ፡ ነው

የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ይባረክ (፬x)
ከመጻሐፍት ፡ በኩር ፡ ታላቅ ፡ መጽሐፍት
የማይለወጥ ፡ የማይሻር
መጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ የአምላኬ ፡ ቃል (፪x)

ከሐዘን ፡ መጽናኛዬ ፡ ቀን ፡ ሙሉ ፡ ትዝታዬ
ሆኖኝ ፡ ወድጄዋለሁ ፡ ዘወትር ፡ አጫዋቼ ፡ ነው
ስስት ፡ ይገስፀኛል ፡ ስዝል ፡ ያበረታኛል
ከስንቁ ፡ በልጦብኛል ፡ ነፍሴን ፡ ሕያው ፡ አድርጓታል

ለእግሬ ፡ ምብራት ፡ ነው
ለመንገዴም ፡ ብርሃን ፡ ነው

ከየት ፡ እንደተገኘሁ ፡ ለምን ፡ በምድር ፡ እንዳለሁ
በኋላም ፡ መድረሻዬን ፡ አሳየኝ ፡ ገልጦ ፡ ዓይኔን
ቁም ፡ ነገረኛ ፡ አድርጐ ፡ ውብ ፡ ዓላማ ፡ አስጨበጠኝ
እንደ ፡ ሌላ ፡ ለውጦ ፡ ከሰውም ፡ ሰው ፡ አረገኝ

የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ይባረክ (፬x)
ከመጻሐፍት ፡ በኩር ፡ ታላቅ ፡ መጽሐፍት
የማይለወጥ ፡ የማይሻር
መጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ የአምላኬ ፡ ቃል (፪x)

እንዱ ፡ ከድኖ ፡ ሲስመው ፡ ሌላው ፡ ሲንተራስበት
አንዱ ፡ ተረት ፡ ሲመስለው ፡ ሌላው ፡ ሲያላግጥ
ለእኔ ፡ ግን ፡ ሆኖኛል ፡ የማይዘለቅ ፡ በረከት (፪x)

ብሰማው ፡ ብሰማው ፡ ማዳምጠው ፡ ማዳምጠው
ሁሌ ፡ አዲስ ፡ ነው ፡ ሁሌ ፡ አዲስ ፡ ነው
ባነበው ፡ ባነበው ፡ ባጠናው ፡ ባጠናው

የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ይባረክ (፬x)
ከመጻሐፍት ፡ በኩር ፡ ታላቅ ፡ መጽሐፍት
የማይለወጥ ፡ የማይሻር
መጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ የአምላኬ ፡ ቃል (፪x)