From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ተሳዳጅ ፡ እፎይ ፡ ሲል ፡ አሳዳጅ ፡ ሬሳበሬሳ
እግዚአብሔር ፡ ክንዱን ፡ ሲያነሳ
ጭንቅ ፡ ውስጥ ፡ አገባቸው ፡ አሳያቸው ፡ ፍዳ ፡ አበሳ
አንሸሽም ፡ ቢሉ ፡ የማይሆን ፡ ሆነ ፡ ነገሩ
ሠራዊቱ ፡ ታወከ ፡ መንከራኩሮቹ ፡ ታሰሩ
ባሕሩ ፡ ከደናቸው ፡ ደግሞ ፡ ሳይተያዩ
እስራኤል ፡ ተሻገረ ፡ ለዘለዓለም ፡ ተለያዩ[1]
አዝ፦ ነገሩ ፡ ተገለበጠ
እግዚአብሔር ፡ ሕዝቡን ፡ አስመለጠ
ነገሩ ፡ ተገለበጠ
አዋጅ ፡ በአዋጅ ፡ ተሻረ
ሞት ፡ በሕይወት ፡ ተቀየረ
እግዚአብሔር ፡ ተነሳ ፡ ንጉሡን ፡ እንቅልፍ ፡ ነሳው
የተዘጋን ፡ መዝገብ ፡ እንዲያገላብጥ ፡ አደረገው
መታሰብ ፡ ሆነና ፡ ሃዘን ፡ በደስታ ፡ ተተካ
ሁኔታው ፡ ሲለወጥ ፡ ሰቃይ ፡ ተሰቃይ ፡ ነው ፡ ለካ
ዋይታና ፡ ስቃይ ፡ ጭንቀት ፡ ሃፍረት ፡ ለጠላታቸው
በአይሁድ ፡ የተድላና ፡ የደስታ ፡ ቀን ፡ ሆነላቸው[2]
አዝ፦ ነገሩ ፡ ተገለበጠ
እግዚአብሔር ፡ ሕዝቡን ፡ አስመለጠ
ነገሩ ፡ ተገለበጠ
አዋጅ ፡ በአዋጅ ፡ ተሻረ
ሞት ፡ በሕይወት ፡ ተቀየረ
ከአምላካቸው ፡ በቀር ፡ ቅዱሳን ፡ ስግደት ፡ አያውቁም
ሚቆጣ ፡ ቢቀጣ ፡ ጣዖትን ፡ ከቶ ፡ አያመልኩም
ሰባት ፡ እጥፍ ፡ ቢነድ ፡ እቶኑ ፡ ቢብስበትም
ያድናል ፡ እርሱ ፡ አንሰግድም ፡ ባያድነንም
የጣሏቸው ፡ ሰዎች ፡ ወሳፈን ፡ ገደላቸው
የልዑል ፡ አምላክ ፡ ባሮች ፡ ክብር ፡ ተጨመረላቸው[3]
አዝ፦ ነገሩ ፡ ተገለበጠ
እግዚአብሔር ፡ ሕዝቡን ፡ አስመለጠ
ነገሩ ፡ ተገለበጠ
አዋጅ ፡ በአዋጅ ፡ ተሻረ
ሞት ፡ በሕይወት ፡ ተቀየረ
|
- ↑ ዘጸዓት ፲፫ ፡ ፲፯ - ፲፬ ፡ ፳፱ (Exodus 13:17 - 14:29)
- ↑ አስቴር ፡ ፮ ፡ ፩ - ፯ ፡ ፲ (Esther 6:1 - 7:10)
- ↑ ዳንኤል ፫ (Daniel 3)