ምህረቱ (Meheretu) - ሮማን ፡ ሳሙኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሮማን ፡ ሳሙኤል
(Roman Samuel)

Roman Samuel 3.jpg


(3)

ነገሩ ፡ ተገለበጠ
(Negeru Tegelebete)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሮማን ፡ ሳሙኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Roman Samuel)

ምህረቱ ፡ እንደ ፡ ደመና (፪x) ፡ ከቦኛል
ልዘምር ፡ የአምላኬን ፡ ምሥጋና (፪x)

የዘወትር ፡ ትዝታው ፡ ማስታወሻው
እኔን ፡ ባየኝ ፡ ቁጥር ፡ ትዝ ፡ የሚለው
የሕይወት ፡ እስትንፋስ ፡ የሆነልኝ
ከምህረቱ ፡ በቀር ፡ ምንም ፡ የለኝ

ጽድቄ ፡ ቅድስናዬ ፡ ቤዛነቴም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
የመዳን ፡ ልብሴ ፡ መጐናጸፊያዬም ፡ እርሱ ፡ ነው

ትልቅ ፡ ልግስናው ፡ ቸርነቱ
ብቃት ፡ ሆኖ ፡ ያቆመኝ ፡ በፊቱ
የማንነቴ ፡ ምንጭ ፡ መገኛዬ
ይቅርታው ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የጌታዬ

ነፍሱን ፡ ሰጥቶ ፡ ነፍሴን ፡ የተቤዛት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
በደሙ ፡ አጥቦ ፡ አዲስ ፡ ንፁህ ፡ ያደረጋት ፡ እርሱ ፡ ነው

የረከሰ ፡ ማንነቴን ፡ ሽሮ
አደፋውን ፡ ታሪኬን ፡ ቀይሮ
በወይኑ ፡ ግንድ ፡ ላይ ፡ የተከለኝ
በአደባባዮቹም ፡ ያበቀለኝ

አክሊል ፡ እንደለበሰ ፡ ሙሽራ ፡ ያስዋበኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ሞገስ ፡ ደም ፡ ግባት ፡ ዝርግፍ ፡ ጌጥ ፡ የሆነኝ ፡ እርሱ ፡ ነው

በምህረቱ ፡ ልጁ ፡ ሆኛለሁ
በምህረቱ ፡ ቤቱ ፡ ኖራለሁ
በምህረቱ ፡ አመልከዋለሁ
በምህረቱ ፡ አገለግላለሁ

ምህረቱ ፡ ሕይወቴ ፡ ምህረቱ ፡ ጉልበቴ
ምህረቱ ፡ ብቃቴ ፡ ምህረቱ ፡ ትምክህቴ
ምህረቱ ፡ እረፍቴ ፡ ምህረቱ ፡ ምችቴ
ምህረቱ ፡ ተድላዬ ፡ ምህረቱ ፡ ጥላዬ