ግቡ ፡ በምሥጋና (Gebu Bemesgana) - ሮማን ፡ ሳሙኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሮማን ፡ ሳሙኤል
(Roman Samuel)

Roman Samuel 3.jpg


(3)

ነገሩ ፡ ተገለበጠ
(Negeru Tegelebete)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሮማን ፡ ሳሙኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Roman Samuel)

እግዚአብሔር ፡ ቸር (፫x)
ምህረቱ ፡ ለዘለዓለም
እውነቱም ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ነውና
ወደ ፡ ደጆቹ ፡ በመገዛት ፡ ኑና
ወደ ፡ አደባባዮቹም ፡ ግቡ ፡ በምሥጋና
ኑና ፡ ግቡ ፡ በምሥጋና

ፀጋው ፡ ያዳናችሁ ፡ አመስግኑት
ፍቅሩ ፡ የገባችሁ ፡ አመስግኑት

ምህረቱን ፡ ተነጋገሩ
ፀጋውን ፡ ተነጋገሩ
ፍቅሩን ፡ ተነጋገሩ
በማስተዋል ፡ ለእርሱ ፡ ዘምሩ

ከሞት ፡ የወጣችሁ ፡ አመስግኑት
ምህረቱን ፡ ያያችሁ ፡ አመስግኑት

ተዓምራቱን ፡ ተነጋገሩ
ጽድቁን ፡ ተነጋገሩ
እውነቱን ፡ ተነጋገሩ
በማስተዋል ፡ ለእርሱ ፡ ዘምሩ

አባት ፡ የሆናችሁ ፡ አመስግኑት
ጉያው ፡ ያሞቃችሁ ፡ አመስግኑት

ቸርነቱን ፡ ተነጋገሩ
ደግነቱን ፡ ተነጋገሩ
አባትነቱን ፡ ተነጋገሩ
በማስተዋል ፡ ለእርሱ ፡ ዘምሩ

ሃሌሉያ (፬x)
በሉ