ደስ ፡ ይበለን (Des Yebelen) - ሮማን ፡ ሳሙኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሮማን ፡ ሳሙኤል
(Roman Samuel)

Roman Samuel 3.jpg


(3)

ነገሩ ፡ ተገለበጠ
(Negeru Tegelebete)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሮማን ፡ ሳሙኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Roman Samuel)

እያንዳንዱ ፡ ቀን ፡ ክፉ ፡ ነው
መልካም ፡ መዓዛ ፡ ጣዕምም ፡ የለው
የትም ፡ ብንሄድ ፡ ምንም ፡ ብንይዝ
ሁሉም ፡ ነገር ፡ አለው ፡ መዘዝ
ነገር ፡ ግን ፡ ዓይኖቻችንን ፡ ወደ ፡ ጌታ ፡ ስናቀና
የሚያስደስተን ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የሚሞላን ፡ በምሥጋና
እስቲ ፡ የላዩን ፡ እናስብ ፡ የምድሩን ፡ እንተወውና

ደስ ፡ ይበለን (፬x)
ሃሴት ፡ እናርግ ፡ ዕልል ፡ እንበል

በምድር ፡ ጥበብ ፡ ጥበበኞች
ሃያላን ፡ ባላባቶች
ብርቱዎችም ፡ ደግሞ ፡ እያሉ
የሰውን ፡ ምስፈርት ፡ የሚያሟሉ
ሥጋን ፡ የለበሰ ፡ ሁሉ ፡ እንዳይመካ ፡ በከንቱ
የዓለምን ፡ ሞኝ ፡ ምናምንቴ ፡ ደካማዎችን ፡ መምረጡ
የሚያስፈነድቅ ፡ ተዓምር ፡ ነው ፡ እንደ ፡ እኛ ፡ ዓይነቱን ፡ መጥራቱ

ደስ ፡ ይበለን (፬x)
ሃሴት ፡ እናርግ ፡ ዕልል ፡ እንበል

በልዩ ፡ ልዩ ፡ ፈተና ፡ ሃዘን ፡ ዛሬ ፡ ቢጐበኘንም
እምነታችን ፡ እንዲነጥር ፡ ፈትና ፡ ቢደርስብንም
ከተዘጋጀልንና ፡ ሊገለጥልን ፡ ካለው ፡ ክብር
ልንወርሰው ፡ ከምንጥብቀው ፡ ከማይጠፋው ፡ ርስታችን ፡ ጋር
ሲመዛዘን ፡ ሥፍራም ፡ የለው ፡ ከቶም ፡ አይገባም ፡ ከቁጥር

እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ደስ ፡ ይበለን
እኛም ፡ ደግሞ ፡ ሕዝቡ ፡ ደስ ፡ ይበለን
በክርስቶስ ፡ ዋጅቶን ፡ ደስ ፡ ይበለን
አርጐናል ፡ ገንዘቡ ፡ ደስ ፡ ይበለን
ከሞት ፡ መንጋጋ ፡ ውስጥ ፡ ደስ ፡ ይበለን
ነጥቆ ፡ አውጥቶናል ፡ ደስ ፡ ይበለን
በክንዱ ፡ መድሃኒት ፡ ደስ ፡ ይበለን
ሕያዋን ፡ አርጐናል ፡ ደስ ፡ ይበለን