ስለተደረገልኝ ፡ በጐነት (Seletederegelegn Begonet) - ሮማን ፡ ሎሬንሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሮማን ፡ ሎሬንሶ
(Roman Lorenso)

Lyrics.jpg


(1)

ጌታ ፡ ብቻ ፡ ታማኝ ፡ ነው
(Gieta Becha Tamagn New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 5:48
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሮማን ፡ ሎሬንሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Roman Lorenso)

አዝ፦ ስለተደረገልኝ ፡ በጐነት
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው (፪x)

ሥራህ ፡ ከአእምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)
አመሰግንሃለው (፮x)

እንደ ፡ ባለማዕረግ ፡ ሰው ፡ ተመልክተኸኝ
የማይገባኝን ፡ ክብርን ፡ ሰጥተኸኝ
የርስትህ ፡ ተካፋይ ፡ የአንተው ፡ አደረከኝ
ለዚህ ፡ ልታበቃኝ ፡ ታዲያ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ
(፪x)

አዝ፦ ስለተደረገልኝ ፡ በጐነት
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው (፪x)

ሥራህ ፡ ከአእምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)
አመሰግንሃለው (፮x)

ማዕበሉ ፡ በዝቶብኝ ፡ እኔን ፡ ሲያንገላታኝ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አልኩኝ ፡ ሥምህን ፡ ጠራሁኝ
እጅህን ፡ ዘርግተህ ፡ በፀናችው ፡ ክንድህ
ታደከኝ ፡ አዳንከኝ ፡ ተባረክ ፡ ልበልህ
(፪x)

አዝ፦ ስለተደረገልኝ ፡ በጐነት
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው (፪x)

ሥራህ ፡ ከአእምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)
አመሰግንሃለው (፮x)

የተገለጠውን ፡ ፍቅርህን ፡ እያየሁ
እንዳልተቀበለ ፡ እንዴት ፡ እሆናለሁ
ምህረት ፡ ማዳንህን ፡ ሁሌ ፡ አወራለሁ
አምላኬ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ፍፁም ፡ አምላክ ፡ ማነው
(፪x)

አዝ፦ ስለተደረገልኝ ፡ በጐነት
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው (፪x)

ሥራህ ፡ ከአእምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)
አመሰግንሃለው (፮x)

በለቅሶ ፡ ሸለቆ ፡ በወሰንከው ፡ ስፍራ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ በረከትህ ፡ በዛ
ከኃይል ፡ ወደ ፡ ኃይል ፡ ያሸጋገርከኝ
ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ሆነልኝ ፡ ኧረ ፡ ምን ፡ ጐደለኝ
(፪x)

አዝ፦ ስለተደረገልኝ ፡ በጐነት
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው
ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው (፪x)

ሥራህ ፡ ከአእምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)
አመሰግንሃለው (፮x)