From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ደመና ፡ ሆኖብኝ ፡ ሁሉ ፡ ነገር ፡ ጨልሞብኝ
ዐይኖቸን ፡ አቅንቸ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ፍረድልኝ ፡ አልኩኝ
(ለካ ፡ ደመናው ፡ ውኃ ያዘለ ፡ ነበር ፡
ደረቀ ፡ ባልኩበት ፡ ዝናቡ ፡ ወረደበት) (፪x)
አዝ፦ ነገር ፡ ለበጐ ፡ ሆኖ ፡ አየሁኝ ፡ ነገረ ፡ ለበጐ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ቅን ፡ ፍርድን ፡ ፈርዶ
ምረቱን ፡ ለእኔ ፡ አውርዶ
እግዚአብሔር ፡ ቅን ፡ ፍርድን ፡ ፈርዶ
ምረቱን ፡ ለእኔ ፡ አግንኖ
ፈተናው ፡ አዝሎኝ ፡ ለመውደቅም ፡ ስንገዳገድ ፡
ባሕሩን ፡ ሲከፍለው ፡ በወጀብ ፡ ውስጥ ፡ አገኘሁኝ ፡ መንገድ
አምላክ ፡ እንደሌለው ፡እንደማንም ፡ ለቆጠረኝ
የምመስክረው ፡ ምናገረው ፡ አለኝ (፪x)
ብቻውን ፡ ታምራት ፡ ድንቅ ፡ ሚያደርግ ፡ ነው
እኔስ ፡ አምላክ ፡ አለኝ ፡ ሁሉ ፡ የተቻለው
ብቻውን ፡ ታምራት ፡ ድንቅ ፡ ሚያደርግ ፡ ነው
እኔስ ፡ ጋሻ፡ አለኝ ፡ሁሉ ፡ የምተማመነው
የምተማመነው ፡ ተስፋ ፡ የማደርገው ፡
ነገሬን ፡ በጊዜው ፡ ውብ ፡ አርጐ ፡ ስሪ ፡ ነው
ያማልክቶቻ ፡ አምላክ ፡ እምላኬ ፡ ኃይለኛ ፡ ነው
በዘመናት ፡ መሃል ፡ ጉልበቱ ፡ ያልዛለው
ቅን ፡ ይፈርዳል ፡ ለተጠጋው ፡ በጊዜው ፡ ደርሶ
ማባበልን ፡ ያውቃል ፡ የፈሰሰን ፡ እንባን ፡ አብሶ
የእኔ ፡ጌታ ፡ ለአኔ ፡ ምርኮዬን ፡ መልሶ
እንደገና ፡ አቆመኝ ፡ ጉልበቴን ፡ አድሶ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ምርኮዬን ፡ መልሶ
እንደገና ፡ አቆመኝ ፡ ሕይወቴን ፡ አድሶ
አዝ፦ ነገር ፡ ለበጐ ፡ ሆኖ ፡ አየሁኝ ፡ ነገረ ፡ ለበጐ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ቅን ፡ ፍርድን ፡ ፈርዶ
ምረቱን ፡ ለእኔ ፡ አውርዶ
እግዚአብሔር ፡ ቅን ፡ ፍርድን ፡ ፈርዶ
ምረቱን ፡ ለእኔ ፡ አግንኖ
|