ማንም ፡ የለም (Manem Yelem) - ሮማን ፡ ሎሬንሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሮማን ፡ ሎሬንሶ
(Roman Lorenso)

Lyrics.jpg


(1)

ጌታ ፡ ብቻ ፡ ታማኝ ፡ ነው
(Gieta Becha Tamagn New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 6:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሮማን ፡ ሎሬንሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Roman Lorenso)

አዝ፦ ማንም ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ በቀር (፪x)
የውስጤን ፡ የልቤን ፡ የሚረዳ ፡ ሚያጽናና
አንተ ፡ ብቻ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ጋሻ ፡ ነህ ፡ መከታ ፡ አሃሃ
አንተ ፡ ብቻ ፡ መጠለያ
ጥላ ፡ ነህ ፡ ከለላ

ሰውማ ፡ ሰው ፡ ነው ፡ ያው ፡ እንደተፈጥሮ
ድጋፍን ፡ ረዳትን ፡ ፈላጊ ፡ ነው ፡ ምርኩዝን
ስለዚህ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ መጠጋት ፡ ያዋጣል
የታመነ ፡ አንተን ፡ ድል ፡ በድል ፡ ይሆናል

አዝ፦ ማንም ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ በቀር (፪x)
የውስጤን ፡ የልቤን ፡ የሚረዳ ፡ ሚያጽናና
አንተ ፡ ብቻ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ጋሻ ፡ ነህ ፡ መከታ ፡ አሃሃ
አንተ ፡ ብቻ ፡ መጠለያ
ጥላ ፡ ነህ ፡ ከለላ

ልብን ፡ ኩላሊትን ፡ ትመረምራለህ
የሰውን ፡ ሁለንተና ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ታውቃለህ
በቅን ፡ የሚፈርድ ፡ አንደአንተ ፡ ማን ፡ አለ
ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ጌታ ፡ ነህ
ጉልበቴ ፡ ዝማሬዬ ፡ ጌታዬ ፡ ኤሄሄ
ጉልበቴ ፡ ዝማሬዬ ፡ የሱሴ
አንተን ፡ ወዳ ፡ ትባርክሃለች ፡ ነፍሴ (፪x)

አዝ፦ ማንም ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ በቀር (፪x)
የውስጤን ፡ የልቤን ፡ የሚረዳ ፡ ሚያጽናና
አንተ ፡ ብቻ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ጋሻ ፡ ነህ ፡ መከታ ፡ አሃሃ
አንተ ፡ ብቻ ፡ መጠለያ
ጥላ ፡ ነህ ፡ ከለላ

ቀን ፡ በደመና ፡ አምድ ፡ መምራትን ፡ ታውቃለህ
ሌሊትም ፡ በእሳት ፡ ጌታ ፡ ትመራለህ
ልዩ ፡ ነው ፡ ስራህ ፡ ግሩም ፡ ጥበቃህ
ተመስገን ፡ ተባረክ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ልበልህ

አዝ፦ ማንም ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ በቀር (፪x)
የውስጤን ፡ የልቤን ፡ የሚረዳ ፡ ሚያጽናና
አንተ ፡ ብቻ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ጋሻ ፡ ነህ ፡ መከታ ፡ አሃሃ
አንተ ፡ ብቻ ፡ መጠለያ
ጥላ ፡ ነህ ፡ ከለላ

የምታስመካ ፡ ጌታ ፡ የምታኮራ ፡ ሆሆሆሆ
የምታስመካ ፡ ጌታ ፡ የምታኮራ ፡ አሃ (፪x)
ጉልበቴ ፡ ዝማሬዬ ፡ ጌታዬ
ጉልበቴ ፡ ዝማሬዬ ፡ የሱሴ
አንተን ፡ ወዳ ፡ ትባርክሃለች ፡ ነፍሴ (፪x)
ጉልበቴ ፡ ዝማሬዬ ፡ ጌታዬ
ጉልበቴ ፡ ዝማሬዬ ፡ የሱሴ
አንተን ፡ ወዳ ፡ ትባርክሃለች ፡ ነፍሴ (፬x)