ለእርሱ ፡ ክብር ፡ ይሁን (Lersu Keber Yehun) - ሮማን ፡ ሎሬንሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሮማን ፡ ሎሬንሶ
(Roman Lorenso)

Lyrics.jpg


(1)

ጌታ ፡ ብቻ ፡ ታማኝ ፡ ነው
(Gieta Becha Tamagn New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:15
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሮማን ፡ ሎሬንሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Roman Lorenso)

ለሚታመኑበት ፡ ተስፋ ፡ ላደረጉት
በጊዜው ፡ ደርሶ ፡ ማሳረፍን ፡ ያውቃል
እግዚአብሔር ፡ አይዋሽም ፡ ለቃሉ ፡ ይተጋል

አዝ፦ ለእርሱ ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር ፡ ዘለዓለም (፪x)
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ከቶ ፡ ማንም ፡ የለም
አሜን ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር ፡ ዘለዓለም (፪x)
ቢቆይ ፡ ቢዘገይም ፡ የሚቀድመው ፡ የለም

ኦሆ ፡ ለልዑል ፡ እግዚአብሔር (፪x)
በሠማይ ፡ በምድር ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር (፪x)

አዝ፦ አሜን ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር ፡ ዘለዓለም (፪x)
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ከቶ ፡ ማንም ፡ የለም
እሰይ ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር ፡ ዘለዓለም (፪x)
ቢቆይ ፡ ቢዘገይም ፡ የሚቀድመው ፡ የለም

እንደ ፡ ትላንትናው ፡ ዛሬም ፡ ድንቅ ፡ ሊሰራ
ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ እርሱ ፡ የሚያቅተው ፡ የለም
ክንዱ ፡ አልደከመም ፡ ብርቱ ፡ ነው ፡ ዘለዓለም

አዝ፦ ለእርሱ ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር ፡ ዘለዓለም (፪x)
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ከቶ ፡ ማንም ፡ የለም
አሜን ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር ፡ ዘለዓለም (፪x)
ቢቆይ ፡ ቢዘገይም ፡ የሚቀድመው ፡ የለም

ፅድቅን ፡ የሚወደው ፡ እግዚአብሔር ፡ ፃድቅ ፡ ነው
ፍርድንም ፡ አያዛባም ፡ ማዳላት ፡ አያውቅም
ሚዛኑ ፡ ትክክል ፡ እርሱ ፡ አይሳሳትም

አዝ፦ ለእርሱ ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር ፡ ዘለዓለም (፪x)
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ከቶ ፡ ማንም ፡ የለም
አሜን ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር ፡ ዘለዓለም (፪x)
ቢቆይ ፡ ቢዘገይም ፡ የሚቀድመው ፡ የለም

ኦሆ ፡ ለልዑል ፡ እግዚአብሔር (፪x)
በሠማይ ፡ በምድር ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር (፪x)

አዝ፦ አሜን ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር ፡ ዘለዓለም (፪x)
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ከቶ ፡ ማንም ፡ የለም
እሰይ ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር ፡ ዘለዓለም (፪x)
ቢቆይ ፡ ቢዘገይም ፡ የሚቀድመው ፡ የለም