From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ዓለሙን ፡ ቢያተርፍ
ነፍሱን ፡ ግን ፡ ባያድን ፡ ምን ፡ ይጠቅመዋል (፬x)
የሰው ፡ ድካሙ ፡ ለሥጋ ፡ ሆኖአል
አይ ፡ ነፍሱ ፡ ግን ፡ በርሃብ ፡ ጠውልጓል
ያከማቻውም ፡ ለሌላ ፡ ይሆናል
የደከመበትን ፡ ሳይበላ ፡ ይቀራል (፪x)
አዝ፦ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ዓለሙን ፡ ቢያተርፍ
ነፍሱን ፡ ግን ፡ ባያድን ፡ ምን ፡ ይጠቅመዋል (፬x)
ፈጣሪህን ፡ አስብ ፡ በጉብዝናህ ፡ ወራት
ኃይል ፡ ከአንተ ፡ እርቆ ፡ ሳይጥልህ ፡ ጉልበት
ትእዛዙን ፡ ጠብቅ ፡ ፍራ ፡ እግዚአብሔርን
ነፍስህ ፡ ሳይመለስ ፡ ሥጋ ፡ ወደ ፡ አፈር (፪x)
አዝ፦ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ዓለሙን ፡ ቢያተርፍ
ነፍሱን ፡ ግን ፡ ባያድን ፡ ምን ፡ ይጠቅመዋል (፬x)
በሕይወት ፡ ዘመንህ ፡ የሚሻልህን
እንዳትረዳው ፡ ጋርዶ ፡ የያዘህን
ዓይንህ ፡ ይገለጥ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ሁሉ
በዚህ ፡ ዓለም ፡ ላይ ፡ ያለው ፡ በሙሉ
በሕይወት ፡ ዘመንሽ ፡ የሚሻልሽን
እንዳትረጂው ፡ ጋርዶ ፡ የያዘሽን
ዓይንሽ ፡ ይገለት ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ሁሉ
ከኢየሱስ ፡ ውጭ ፡ ያለው ፡ በሙሉ
አዝ፦ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ዓለሙን ፡ ቢያተርፍ
ነፍሱን ፡ ግን ፡ ባያድን ፡ ምን ፡ ይጠቅመዋል (፬x)
|