From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x)
ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x)
ለሰራዊት ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር (፪x)
በነጩ ፡ ዙፋን ፡ ተቀምጠሃል
አክሊላቸውን ፡ ያወሩልሃል
ሁሉን ፡ ፈጥረሃል ፡ ፈቃድህ ፡ ሆኗል
እጅግ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ማን ፡ ይመስልሃል
አዝ፦ ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x)
ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x)
ለሰራዊት ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር (፪x)
መልክህ ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ አንተ ፡ ትልቁ
. (1) .
ቀስተደመና ፡ ማዕረግህ ፡ ዙሪያህ
ከቦ ፡ ይልሃል ፡ ኃያል ፡ ቅዱስ ፡ ነህ
አዝ፦ ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x)
ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x)
ለሰራዊት ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር (፪x)
እልፍ ፡ ጊዜ ፡ እልፍ ፡ ሺህም ፡ ጊዜ ፡ ሺህ
የምትመለክ ፡ በመላእክትህ
በኪሩቤል ፡ ላይ ፡ ምትመላለስ
እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ዘላለም ፡ ቅዱስ
አዝ፦ ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x)
ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x)
የሰራዊት ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር (፪x)
ነገሥታት ፡ ሲያልፉ ፡ ሲለዋወጡ
አንተ ፡ ግን ፡ ሕያው ፡ ሁልጊዜ ፡ ብርቱ
በቅንድቦችህ ፡ ሰውን ፡ መርማሪ
መሳይ ፡ የሌለህ ፡ ተወዳዳሪ
አዝ፦ ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x)
ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x)
የሰራዊት ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር (፪x)
ከእስራት ፡ ፈቺ ፡ ቀንበር ፡ ሰባሪ
በጽድቅ ፡ ዙፋን ፡ ዘላለም ፡ ኗሪ
ማደሪያህ ፡ ቅዱስ ፡ አንተ ፡ ቅዱስ ፡ ነህ
ሰማይ ፡ ምድር ፡ ሲያልፍ ፡ በክብር ፡ አለህ
አዝ፦ ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x)
ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x)
የሰራዊት ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር (፮x)
|