ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር (Lenie Yaleh Feqer) - ረዳ ፡ አብርሃም

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ረዳ ፡ አብርሃም
(Redda Abraham)

Lyrics.jpg


(1)

አልጥልህም ፡ አልተውህም
(Altelehem Altewehem)

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:48
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የረዳ ፡ አብርሃም ፡ አልበሞች
(Albums by Redda Abraham)

አዝ፦ ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው
ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነው
አይምሮን ፡ ያልፋል ፡ እጅግ ፡ ይበዛል
እንዴት ፡ ሊነገር ፡ ይችላል
በምን ፡ ሊገለጽ ፡ ይችላል
ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ልዩ ፡ ነው

መስቀል ፡ ተሸክመህ ፡ ደፋ ፡ ቀና ፡ ብለህ
በፈጠርከው ፡ ፍጥረት ፡ እየተንገላታህ
እጅጉን ፡ ተንቀህ ፡ በጣምም ፡ ተዋርደህ
እኔን ፡ አድነሃል ፡ ይግነን ፡ ታላቅ ፡ ስምህ (፪x)

አዝ፦ ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው
ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነው
አይምሮን ፡ ያልፋል ፡ እጅግ ፡ ይበዛል
እንዴት ፡ ሊነገር ፡ ይችላል
በምን ፡ ሊገለጽ ፡ ይችላል
ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ልዩ ፡ ነው

ለአይምሮ ፡ በሚክብድ ፡ በዘግናኝ ፡ ሁኔታ
እጅህና ፡ እግርህ ፡ በሚስማር ፡ ተመታ
ያለ ፡ እንዳች ፡ ርህራሄ ፡ ኢየሱስ ፡ በጭካኔ
ግፍ ፡ አደረሱብህ ፡ ተሰቃየህ ፡ ለእኔ (፪x)

አዝ፦ ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው
ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነው
አይምሮን ፡ ያልፋል ፡ እጅግ ፡ ይበዛል
እንዴት ፡ ሊነገር ፡ ይችላል
በምን ፡ ሊገለጽ ፡ ይችላል
ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ልዩ ፡ ነው

ከወንበዴዎች ፡ ጋር ፡ ሰቀሉህ ፡ ኢየሱስ
ከላይ ፡ የወረድህ ፡ ሳለህ ፡ የዓለም ፡ ንጉስ
ሆምጣጤም ፡ አጠጡህ ፡ ጨከኙ ፡ በብዙ
ጌትነትህ ፡ የታል ፡ እያሉ ፡ እያፌዙ (፪x)

አዝ፦ ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው
ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነው
አይምሮን ፡ ያልፋል ፡ እጅግ ፡ ይበዛል
እንዴት ፡ ሊነገር ፡ ይችላል
በምን ፡ ሊገለጽ ፡ ይችላል
ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ልዩ ፡ ነው

በእንጨት ፡ ተሰቅለህ ፡ እንደ ፡ መርገም ፡ ሰው
ለጠላቶችህ ፡ ማለድኽ ፡ ፍቅርህ ፡ ሰፊ ፡ ነው
ተፈጸመም ፡ አልህ ፡ ነፍስህን ፡ ሰጠህ ፡ ለኔ
ከፍ ፡ በል ፡ ተባረክ ፡ ዘላለም ፡ መድህኔ (፪x)

አዝ፦ ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው
ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነው
አይምሮን ፡ ያልፋል ፡ እጅግ ፡ ይበዛል
እንዴት ፡ ሊነገር ፡ ይችላል
በምን ፡ ሊገለጽ ፡ ይችላል
ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x)