From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ ፡ እንዲሁም ፡ ጥበቃህ
ደግሞም ፡ ቸርነትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝተዋል (፪x)
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ ፡ እንዲሁም ፡ ጥበቃህ
ደግሞም ፡ ቸርነትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝተዋል (፪x)
ቸርነትህ ፡ ምህረትህ ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ
ስለሚጠብቁኝ ፡ በመሆን ፡ ከጐኔ
አልጠፋሁም ፡ ኢየሱስ ፡ አለሁኝ ፡ በቤትህ
ስዘምር ፡ እኖራለሁ ፡ ለታላቁ ፡ ስምህ
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ ፡ እንዲሁም ፡ ጥበቃህ
ደግሞም ፡ ቸርነትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝተዋል (፪x)
ጠላቴ ፡ ሊያጠፋኝ ፡ ጦሩን ፡ ሲወረውር
ከግድግዳ ፡ ጋርም ፡ እኔኑ ፡ ሊያጣብቅ
ነገር ፡ ግን ፡ አልሆነም ፡ ምህረትህ ፡ ቀደመ
የዲያብሎስ ፡ ሃሳብ ፡ እቅዱ ፡ ባከነ
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ ፡ እንዲሁም ፡ ጥበቃህ
ደግሞም ፡ ቸርነትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝተዋል (፪x)
በምህረትህ ፡ ብዛት ፡ ቤትህ ፡ እገባለሁ
አምልኮ ፡ ዝማሬ ፡ ስግደት ፡ እየሰጠሑ
ገናም ፡ እኖራለሁ ፡ ስለምትጠብቀኝ
እስከ ፡ ዓለም ፡ ፍጻሜ ፡ ሰለማትተወኝ
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ ፡ እንዲሁም ፡ ጥበቃህ
ደግሞም ፡ ቸርነትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝተዋል (፪x)
አግዚአብሄር ፡ ታላቅ ፡ ባለብዙ ፡ ምህረት
ልጅህ ፡ ስላረከኝ ፡ በብዙ ፡ ቸርነት
እኔም ፡ በዝማሬ ፡ ምህረትህን ፡ አነግራለሁ
እስከምትወስደኝ ፡ አገለግላለሁ
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ ፡ እንዲሁም ፡ ጥበቃህ
ደግሞም ፡ ቸርነትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝተዋል (፪x)
በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ ሁሉን ፡ በምትችለው
ባንተ ፡ ስለምኖር ፡ ምህረትህ ፡ በበዛው
የሚያስፈራኝ ፡ የለም ፡ ከጠላትህ ፡ መንደር
አንተ ፡ ስለጣልከልኝ ፡ ወደ ፡ ጥልቁ ፡ ባሕር
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ ፡ እንዲሁም ፡ ጥበቃህ
ደግሞም ፡ ቸርነትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝተዋል (፪x)
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ ፡ እንዲሁም ፡ ጥበቃህ
ደግሞም ፡ ቸርነትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝተዋል (፪x)
ልዑል ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ ፡ እንዲሁም ፡ ጥበቃህ
ደግሞም ፡ ቸርነትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝተዋል (፪x)
|