እግዚአብሔር ፡ ጸሎትን ፡ ይሰማል (Egziabhier Tseloten Yesemal) - ሰሜን ፡ ናዝሬት ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ ቤ/ክ ፡ ልጆች ፡ ክፍል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰሜን ፡ ናዝሬት ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ ቤ/ክ ፡ ልጆች ፡ ክፍል
(North Nazareth Meserete Kristos Church Children)

Lyrics.jpg


(1)

እኔ ፡ የማመልከው
(Enie Yemamelkew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰሜን ፡ ናዝሬት ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ ቤ/ክ ፡ ልጆች ፡ ክፍል ፡ አልበሞች
(Albums by North Nazareth Meserete Kristos Church Children)

በሰማያት ፡ የምትኖር ፡ አባታችን ፡ ሆይ
ስምህ ፡ ይቀደስ ፡ መንግሥትህ ፡ ትምጣ
ፈቃድህ ፡ በሰማይ ፡ እንደሆነ
እንዲሁም ፡ በምድር ፡ ትሁን
የዕለት ፡ እንጀራችንን ፡ ዛሬ ፡ ስጠን
እናም ፡ የበደሉልን ፡ ይቅር ፡ እንደምንል
በደላችንን ፡ ይቅር ፡ በለን
ከክፉ ፡ አድነን ፡ እንጂ ፡ ወደፈተናም ፡ አታግባን
መንግሥት ፡ የአንተ ፡ ናትና
ሃይልም ፡ ክብርም ፡ ለዘለዓለም ፡ አሜን (፪x)

አዝእግዚአብሔር ፡ ጸሎትን ፡ ይሰማል (፬x)
ኦ ፡ ጌታ ፡ ጸሎትን ፡ ይሰማል
ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰምቶ ፡ ይመልሳል

ሃናም ፡ ስትጸልይ ፡ ሰምቷታል
ልጅን ፡ ሰጥቷታል
እኛም ፡ ስንጸልይ ፡ ሰምቶናል
ድንቅ ፡ አድርጐልናል

አዝእግዚአብሔር ፡ ጸሎትን ፡ ይሰማል (፬x)
ኦ ፡ ጌታ ፡ ጸሎትን ፡ ይሰማል
ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰምቶ ፡ ይመልሳል

ኤልያስ ፡ ሲጸልይ ፡ ሰቶታል
ሰማይ ፡ ተዘግቷል ፡ ደግሞም ፡ ተከፍቷል
እናንተም ፡ ጸልዩ ፡ ይሰማል
ድንቅን ፡ ያደርጋል

አዝእግዚአብሔር ፡ ጸሎትን ፡ ይሰማል (፬x)
ኦ ፡ ጌታ ፡ ጸሎትን ፡ ይሰማል
ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰምቶ ፡ ይመልሳል

አባዬም ፡ ሲጸልይ ፡ ሰምቶታል ፡ መልሶለታል
እማዬም ፡ ስትጸልይ ፡ ሰምቷታል ፡ መልሶላታል
እናንተም ፡ ጸልዩ ፡ ይሰማል
ድንቅን ፡ ያደርጋል

አዝእግዚአብሔር ፡ ጸሎትን ፡ ይሰማል (፬x)
ኦ ፡ ጌታ ፡ ጸሎትን ፡ ይሰማል
ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰምቶ ፡ ይመልሳል

ኦ ፡ ጌታ ፡ ጸሎትን ፡ ይሰማል
ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰምቶ ፡ ይመልሳል