የሰላም ፡ አምላክ (Yeselam Amlak) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(3)

ላይህ ፡ ናፍቃለሁ
(Layeh Nafeqalehu)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 7:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

አመንዝራዪቷ ፡ እንዲፈረድባት ፡
በጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ፊት ፡ አምጥተው ፡ አቆሟት
ጌታ ፡ ግን ፡ ከእናንተ ፡ ሃጥያት ፡ የሌለበት
አላቸው ፡ ይህቺን ፡ ሴት ፡ በድንጋይ ፡ ይውገራት
ሁሉም ፡ ህሊናቸው ፡ ስለወቀሳቸው
ወጡ ፡ ኢየሱስ ፡ ቀረ ፡ ያለሃጥያት ፡ ለብቻው
ያቺ ፡ ሴት ፡ በፊቱ ፡ ቆማ ፡ ሲመለከት
እኔ ፡ አልፈርድብሽም ፡ ደግመሽ ፡ አጢያት ፡ አትስሪ ፡ አላት
የኢየሱስ ፡ ፍቅሩ ፡ ምህረቱ ፡ አዳናት
በእግሩ ፡ ስር ፡ አረፈች ፡ ሰላም ፡ ስለሆናት
ዋጋው ፡ እጅግ ፡ የብዛ ፡ ሽቶ ፡ የሞላበት
የአልባጥሮስ ፡ ብልቃት ፡ ሰብራ ፡ አፈሰሰችለት ፡

 የሰላም ፡ አምላክ ፡ የሰላም ፡ ንጉሥ
 ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ኦ ፡ ኢየሱስ
 ምልካም ፡ ነህ ፡ ፍቅር ፡ ነህ
 ለሰው ፡ ሁሉ ፡ ትሆናለህ
 መልካም ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ፍቅር ፡ ነህ ፡
 ለሰው ፡ ሁሉ ፡ ፡ መድሃኒት ፡ ነህ

ርኩስ ፡ መንፈስ ፡ ይዞት ፡ ብረት ፡ የማያስረው
ከሰው ፡ ተለይቶ ፡ መቃብር ፡ ሚኖረው
የሰላሙ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ ፡ ሲገናኘው
እርኩስ ፡ መንፈሱን ፡ አዞ ፡ ገስጾ ፡ አስወጣው
የዚህም ፡ ሰው ፡ ልቡ ፡ ተመለሰለት
ከሰው ፡ ቀላቀለው ፡ ጌታ ፡ ነጻ ፡ አድርጐት
ሚቀርበው ፡ ያልነበረውን ፡ ምስራች ፡ ነጋሪ
ኢየሱስ ፡ አደረገው ፡ የእርሱን ፡ ድንቅ ፡ አብሳሪ
ሽባው ፡ ተፈውሶ ፡ እውሮችም ፡ አይተው
ደንቆሮችም ፡ ሰምተው ፡ ለምጻሞችም ፡ ነጽተው
ነፍሳቸውም ፡ ድና ፡ ከስውም ፡ እኩል ፡ ሆነው
ከበሩ ፡ በኢየሱስ ፡ ፡ ሆኖ ፡ የተጻፈው

ልሸከመው ፡ ማልችለውን ፡ ከባዱን ፡ ኃጢአቴን ፡
የሰሱስ ፡ ተሸክሞ ፡ ሞቶልኛል ፡ ሞቴን
እዳዬን ፡ ከፍሎልኝ ፡ ደሙ ፡ ደምስሶልኝ
በዘለዓለም ፡ መጽሐፍ ፡ ስሜ ፡ ተጻፈልኝ
የማይጠፋ ፡ ደስታ ፡ የማይወሰድብኝ
ፈሰሰ ፡ በልቤ ፡ ኢየሱስ ፡ ፈውሶኝ
የእርሱ ፡ የሆነውን ፡ የዘላላም ፡ ሰላም
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰጠኝ ፡ ያልሆነ ፡ ከዚህ ፡ ዓለም
የሰላሙ ፡ ንጉሥ ፡ የሰላሙ ፡ አለቃ
ንጉሤ ፡ ሆናልኝ ፡ መቅበዝዜ ፡ አበቃ
እፎይ ፡ አልኩ ፡ አረፍኩኝ ፡ እኔም ፡ እንደ ፡ ማሪያም
ኢየሱስ ፡ ስለሆነኝ ፡ የሕይወቴ ፡ ሰላም