ኦ ፡ ምሥጋና (O Mesgana) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(3)

ላይህ ፡ ናፍቃለሁ
(Layeh Nafeqalehu)

ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 3:29
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

ኦ ፡ ምሥጋና ፡ ለጌታ ፡ ኦ ፡ ምሥጋና ፡ ለኢየሱስ
ኦ ፡ ምሥጋና ፡ አሜን ፡ ለአምላኬ ፡ ይገባዋልና (፪x)

ጠላት ፡ ዙሪዬን ፡ ሲከበኝ
ወደ ፡ አምላኬ ፡ አነባሁኝ
መብረቁን ፡ ከሰማይ ፡ ላከ
የሚያውከኝን ፡ አወክ
የሚገፋኝን ፡ እየገፋ
ጌታ ፡ ድንበሬን ፡ አሰፋ
ያስጨነቀኝ ፡ እስጨነቀ
ስሙን ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ አደመቀ

ጠላት ፡ በቃሉ ፡ ሲያደናግረኝ
ከያዝኩት ፡ እውነት ፡ ሊያላቅቀኝ
አምላኬ ፡ አይቶ ፡ ሳቀበት ፡
መታሰቢያውን ፡ ሁሉ ፡ አጠፋበት
ግራ ፡ ያጋባኝ ፡ ተበተነ
እንደ ፡ ገላባ ፡ በነነ
ወጥመድ ፡ መንገዴን ፡ ዘርግቶበት
በላዩ ፡ ወድቆ ፡ ተያዘበት

የክፉውን ፡ ውሸት ፡ ገለበጠ
የእግዚአብሔር ፡ እውነት ፡ ተገለጠ
በቤቴ ፡ ሰላም ፡ እረፍት ፡ ሆነ
የሱስ ፡ በኑሮዬ ፡ ገነነ
የሱስ ፡ በልቤ ፡ ስፍራ ፡ ያዘ
ንፋሱ ፡ ፀጥ ፡ አለ ፡ ታዘዘ
ማህበል ፡ ወጀቡን ፡ ገሰፀው
መርከቡን ፡ በሰላም ፡ አስኬደው