ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ (Eyesus Ante Neh) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(3)

ላይህ ፡ ናፍቃለሁ
(Layeh Nafeqalehu)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 6:27
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ
 ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እኔ ፡ ደስ ፡ ያሰኘህ
 ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ
 ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እኔ ፡ ደስ ፡ ያሰኘህ

አድነኸኛል ፡ ከሞት ፡
መጥተህ ፡ ወዳላሁበት
ከዚህ ፡ የተነሳ ፡ አረፍኩኝ ፡
ይኸው ፡ ምሥጋንና ፡ አመጣሁኝ
 ፡ ምሥጋና ፡ ለማዳንህ ፡ ምሥጋና ፡ ይኸው
 ፡ ምሥጋና ፡ ለማዳንህ ፡ ምሥጋና
 ፡ ተባረክ ፡ ጌታዬ ፡ ተባረክ ፡ ኦሆ
 ፡ ተባረክ ፡ አምላኬ ፡ ተባረክ

ተጨንቀኽልኝ ፡ ስለኔ ፡
ሰላምን ፡ ሰጠኸኝ ፡ ለኔ
እንደ ፡ ወንዝ ፡ በልቤ ፡ ፈሳል
ይኸው ፡ ምሥጋናዬን ፡ ተቀበል
 ፡ ምሥጋና ፡ ለሰላምህ ፡ ምሥጋና ፡ ይኸው
 ፡ ምሥጋና ፡ ለሰላምህ ፡ ምሥጋና
 ፡ ተባረክ ፡ ጌታዬ ፡ ተባረክ ፡ ኦሆ
 ፡ ተባረክ ፡ አምላኬ ፡ ተባረክ

በልቅሶ ፡ በሃዘን ፡ ፈንታ
አስታጥቀኸኛል ፡ ደስታ
መከራን ፡ በአንተ ፡ ረስቼ ፡
ይኸው ፡ ምጋናህን ፡ አብዘቼ
 ፡ ምሥጋና ፡ ለደስታህ ፡ ምሥጋና ፡ ይኸው
 ፡ ምሥጋና ፡ ለደስታህ ፡ ምሥጋና
 ፡ ተባረክ ፡ ጌታዬ ፡ ተባረክ ፡ ኦሆ
 ፡ ተባረክ ፡ አምላኬ ፡ ተባረክ

ምንም ፡ አያሻኝ ፡ ረክቼ
ጌታን ፡ አንተን ፡ ተጠግቼ
ጌታ ፡ በልቤ ፡ ከብረሃል
አፌም ፡ ምግናህን ፡ ያወራል
 ፡ በዚህች ፡ ዕውቀት ፡ እንዲህ ፡ ካረካኸኝ
 ፡ ብዙ ፡ ባውቅህ ፡ ምን ፡ እሆናለሁኝ
 ፡ ናፍቃለሁ ፡ ጌታ ፡ ብዙ ፡ ላውቅህ
 ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ስግደት ፡ ላመጣልህ
 ፡ በቀረው ፡ ዘመኔ ፡ ውርስ ፡ የምፈልገው
 ፡ ብር ፡ ወርቅን ፡ አይደለም ፡ ጌታዬ ፡ አንተን ፡ ነው
 ፡ ዛሬ ፡ ያለኸን ፡ አንተ ፡ ምሻውም ፡ አንተን ፡ ነው
 ፡ ነገም ፡ ከዛ ፡ ወዲያ ፡ መሻቴ ፡ አንተን ፡ ነው