እሰይ ፡ አባት ፡ አለን ፡ በሰማይ (Esey Abat Alen Besemay) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(3)

ላይህ ፡ ናፍቃለሁ
(Layeh Nafeqalehu)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 3:17
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

እሰይ ፡ እሰይ ፡ እሰይ
 እሰይ ፡ እሰይ ፡ እሰይ
 እሰይ ፡ እሰይ ፡ እሰይ
 አባት ፡ አለን ፡ በሰማይ

ወፎች ፡ ሚመግባቸው ፡
አበቦችን ፡ ያሳመራቸው
ከእነርሱ ፡ አስበልጦናል ፡
አባታችን ፡ ያስብልናል
ጠላቶች ፡ ሳለን ፡ የወደደን
በውድ ፡ ልጁ ፡ የታረቀን
ስንለምነው ፡ ይሰማናል
መንፈሱን ፡ ያፈስልናል

እኛ ፡ ክፉዎች ፡ ስንሆን
ልጆቻንን ፡ ከወደድን
እርሱ ፡ የሰማይ ፡ አባታችን
ደግ ፡ ነው ፡ የሚያስብልን
እጅግ ፡ የሚምር ፡ የሚራራ
አባት ፡ አለ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ
እርሱ ፡ ነው ፡ የእኛ ፡ አባታችን
ሚያስብ ፡ ሚጠነቀቅልን

 እሰይ ፡ እሰይ ፡ እሰይ
 እሰይ ፡ እሰይ ፡ እሰይ
 እሰይ ፡ እሰይ ፡ እሰይ
 አባት ፡ አለን ፡ በሰማይ
 አሜን ፡ አሜን ፡ አሜን
 አሜን ፡ አሜን ፡ አሜን
 አሜን ፡ አሜን ፡ አሜን
 በሰማይ ፡ አባት ፡ አለን

አባ ፡ አባ ፡ እንድንለው
መንፈሱን ፡ በእኛ ፡ አፈሰሰው
ልጆቹ ፡ አድርጐናል
አባት ፡ አለን ፡ ያስብልናል
ፍጻሜና ፡ ተስፋ ፡ ሰጭያችን
እርሱ ፡ የሰላም ፡ አምላካችን ፡
እግዚአብሔር ፡ ይወዳናል
ክማንም ፡ ይልቅ ፡ ቀርቦናል

 እሰይ ፡ እሰይ ፡ እሰይ
 እሰይ ፡ እሰይ ፡ እሰይ
 እሰይ ፡ እሰይ ፡ እሰይ
 አባት ፡ አለን ፡ በሰማይ
 አሜን ፡ አሜን ፡ አሜን
 አሜን ፡ አሜን ፡ አሜን
 አሜን ፡ አሜን ፡ አሜን
 በሰማይ ፡ አባት ፡ አለን