እንደ ፡ አምላክነትህ ፡ ልፍራህ (Ende Amlakeneteh Lefrah) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(3)

ላይህ ፡ ናፍቃለሁ
(Layeh Nafeqalehu)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 6:03
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

እስቲ ፡ እንደ ፡ አምላክንትህ ፡ እኔ ፡ ልፍራህ
እስቲ ፡ እንደ ፡ አባትህ ፡ ላክብርህ
እስቲ ፡ እንደ ፡ ንጉሥነትህ ፡ ልገዛልህ
እስቲ ፡ እንደ ፡ አዳኝነትህ ፡ ልውደድህ

እንደ ፡ አምልካንትህ ፡ እኔ ፡ ልፍራህ ፡ ላምልክህ
እርሱን ፡ ብቻ ፡ ይሁን ፡ የምጠራው ፡ ቅዱስ ፡ ስምህ
ቀኑን ፡ ሁሉ ፡ አንተን ፡ እየፈራሁኝ ፡ ልኑር
እንተ ፡ ብቻ ፡ ለኔ ፡ አምላኬ ፡ እግዚአብሔር

እንደ ፡ አባትነህ ፡ ላክብርህ ፡ ልቅረብህ
ደስ ፡ ያሚያሰኘኝም ፡ ይሁንልኝ ፡ ፈቃድህ
አባ ፡ አባ ፡ ብዬ ፡ እንደ ፡ አባቴ ፡ ልጠይቅህ
የከበረ ፡ ይሁን ፡ በእኔም፡ ዘንድ ፡ ስጦታህ

እንደ ፡ ንጉሥነትህ ፡ ልታዛዝህ ፡ ልገዛልህ ፡
የሚያስተዳድረኝ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን ፡ ትህዛዝህ
ሥልጣንህም ፡ ይግዛኝ ፡ ፡ ያንበርክከኝ ስረአት ፡ ያሲዘኝ
በፊትህ ፡ ልዋረድ ፡ ክብርህም ፡ ያስጐንብስኝ

እንደ ፡ አዳኝነትህ ፡ ልወደድህ ፡ ልቀኝልህ
ክብሬ ፡ ትዋረድልህ ፡ ያለኝን ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ልስጥህ
ነፍሴም ፡ ተጠቅልላ ፡ እንተን ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ ትበል
በእንተ ፡ ደስ ፡ እያላት ፡ ትጠንልህ ፡ ቸል ፡ ሳትል