የሠማይ ፡ አምላክ (Yesemay Amlak) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(1)

ኢየሱስ ፡ ፍቅር
(Eyesus Feqer)

ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

የሰማይ ፡ አምላክ ፡ የሰራዊት ፡ ጌታ
ነፍሴ ፡ ታመስግንህ ፡ ጥዋትና ፡ ማታ
ቅኔ ፡ ልቀኝልህ ፡ ልቅረብ ፡ በዝማሬ
በአንተ ፡ ስራ ፡ ነው ፡ እዚህ ፡ ያለሁት ፡ ዛሬ

ዋጋ ፡ ያልነበረኝ ፡ ከንቱ ፡ የተረሳሁ
አምላኬን ፡ የማላውቅ ፡ ነበርኩ ፡ እረኛ ፡ ያጣሁ
በከበረው ፡ ልጅህ ፡ በደምህ ፡ ገዝተኸኝ
አምላኬ ፡ ሆንክልኝ ፡ ልጅህ ፡ አደረከኝ

መች ፡ አምላኬ ፡ ብቻ ፡ አበቴም ፡ ወዳጄም
አስተማሪዬም ፡ ነው ፡ ጠባቂ ፡ እረኛዬም
ሳዝን ፡ አጽናኜ ፡ ነው ፡ ሳጠፋም ፡ ቀጪዬ
በመንገዴ ፡ ሁሉ ፡ ብርሃኔ ፡ መሪዬ

ሞገሴም ፡ ነው ፡ ክብሬ ፡ ዕውቀቴ ፡ ጥበቤ
መብራቴ ፡ ነው ፡ ለኔ ፡ ሆኖ ፡ ካጠገቤ
ቢያመኝ ፡ መድሃኒቴ ፡ ወዜም ፡ ደም ፡ ግባቴ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ለኔ ፡ ዋስትና ፡ ለሕይወቴ

የድህንነት ፡ ዋጋ ፡ ለኔ ፡ የከፈለው
ውድ ፡ ነው ፡ ክቡር ፡ ነው ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው
መቼ ፡ በዚህ ፡ ብቻ ፡ ተወኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ለሥጋም ፡ ለነፍሴም ፡ ሆነልኝ ፡ እርካታ