መልካም ፡ እረኛ (Melkam Eregna) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(1)

ኢየሱስ ፡ ፍቅር
(Eyesus Feqer)

ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

መልካም ፡ እረኛ ፡ መተማመኛ
 ኢየሱስ ፡ ሆንልኝ ፡ ለኔ ፡ ጉዳኛ
 ስጠማ ፡ ውሃዬ ፡ ስራብም ፡ ምግቤ
 ጠባቂዬ ፡ ነው ፡ ሆኖ ፡ አጠገቤ

ነፍሱን ፡ ስለኔ ፡ ሰውቶልኛል
ከክብሩ ፡ ወርዶ ፡ ተሰቅሎልኛል
እንደርሱ ፡ ያለ ፡ ወዳጅ ፡ ከየት ፡ አገኛለሁ
አዳኜን ፡ ውዴን ፡ እውደዋለሁ

ዳገት ፡ ስወጣ ፡ አብሮኝ ፡ ይወጣል
ሸለቆ ፡ ስወርድ ፡ እርሱ ፡ ያወጣኛል
ሳዝን ፡ ስተክዝ ፡ ያበረታኛል
ባሴት ፡ በደስታ ፡ ልቤን ፡ ይሞላል

በመስቀል ፡ ጉዞ ፡ በፈተናዬ
ይመራኛል ፡ ሆኖ ፡ መሪዬ
በምድር ፡ ኑሮ ፡ በመከራዬ
እርሱ ፡ ያጸናኛል ፡ ሆኖ ፡ አልኝታዬ

በለምለሙ ፡ መስክ ፡ ያስድረኛል
በእረፈት ፡ ውኃ ፡ ዘንድ ፡ ሁሌ ፡ ይመራኛል
ብትር ፡ ምርኩዝህ ፡ ሁሌ ፡ ያጽናኑኛል
አንት ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ነህ ፡ ምን ፡ ያስፈራኛል