ማዳኑን ፡ አይቻለሁ (Madanun Ayechalehu) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(1)

ኢየሱስ ፡ ፍቅር
(Eyesus Feqer)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 6:01
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

ከክፉው ፡ ካስፈሪው ፡ ኢየሱስ ፡ ታድጐኛል
ከጨለማ ፡ አውጥቶ ፡ ብርሃን ፡ ሆኖልኛል
በጠላቴም ፡ ፊት ፡ ዘይት ፡ ቀብቶኛል
ከሳሼን ፡ ጥሎልኝ ፡ እኔን ፡ አክብሮኛል

አዝ፦ ማዳኑን ፡ ማዳኑን ፡ አይቻለሁ (፪x)
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ አዳኜ ፡ ነው
ጥበቃው ፡ ጥበቃው ፡ በላዬ ፡ ላይ (፪x)
ሆኖልኛልና ፡ ከሰማይ

በባዕድ ፡ አገር ፡ ወገን ፡ አባት ፡ ሆኖልኛል
በአለቆችም ፡ ፊት ፡ ሞገስ ፡ ሆንልኛል
ወንዙን ፡ ማዕበሉን ፡ እርሱ ፡ አሳልፎኛል
በዚህ ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ ጥላ ፡ ሆንልኛል

አዝ፦ ማዳኑን ፡ ማዳኑን ፡ አይቻለሁ (፪x)
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ አዳኜ ፡ ነው
ጥበቃው ፡ ጥበቃው ፡ በላዬ ፡ ላይ (፪x)
ሆኖልኛልና ፡ ከሰማይ

ሥሙ ፡ እንደሚፈስ ፡ ዘይት ፡ ሆኖልኛል
ልቤን ፡ በደስታ ፡ አፌን ፡ በሳቅ ፡ ሞልቷል
ሕጉ ፡ ለእግሬ ፡ መብራት ፡ ብርሃን ፡ ሆኖልኛል
እንዳልሰናከል ፡ ኢየሱስ ፡ ጠብቆኛል

አዝ፦ ማዳኑን ፡ ማዳኑን ፡ አይቻለሁ (፪x)
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ አዳኜ ፡ ነው
ጥበቃው ፡ ጥበቃው ፡ በላዬ ፡ ላይ (፪x)
ሆኖልኛልና ፡ ከሰማይ

ምህረት ፡ ቸርነቱ ፡ ፍቅሩ ፡ እኔን ፡ ከቦኛል
የማዳኑ ፡ ሥራ ፡ እጅግ ፡ በዝቶልኛል
ስተኛ ፡ ቀስቅሶኝ ፡ ስዝል ፡ ደግፎኛል
አለቱ ፡ ኢየሱስ ፡ በእጁ ፡ ይዞኛል

አዝ፦ ማዳኑን ፡ ማዳኑን ፡ አይቻለሁ (፪x)
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ አዳኜ ፡ ነው
ጥበቃው ፡ ጥበቃው ፡ በላዬ ፡ ላይ (፪x)
ሆኖልኛልና ፡ ከሰማይ

ለውለታው ፡ ሁሉ ፡ ምን ፡ እመልሳለሁ
ባወራው ፡ ባወራው ፡ አያልቅም ፡ ብዙ ፡ ነው
በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ ለእርሱ ፡ ዘምራለሁ
ተመስገን ፡ እያልኩኝ ፡ እቀኝለታለሁ

አዝ፦ ማዳኑን ፡ ማዳኑን ፡ አይቻለሁ (፪x)
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ አዳኜ ፡ ነው
ጥበቃው ፡ ጥበቃው ፡ በላዬ ፡ ላይ (፪x)
ሆኖልኛልና ፡ ከሰማይ (፪x)