ክበር ፡ በሉት ፡ ኢየሱስን (Keber Belut Eyesusen) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(1)

ኢየሱስ ፡ ፍቅር
(Eyesus Feqer)

ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

ለናዝሬት ፡ ኢየሱስ ፡ እንደበግ ፡ ለታረደው
በደሙ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ሰዎችን ፡ ለዋጀው
ለአምላክ ፡ መንግሥትና ፡ ካህናት ፡ ላደረገው ፡
በረከትና ፡ ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው
  ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ኢየሱስን
  ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡

ያለና ፡ የነበር ፡ የሚመጣው ፡ ሁሉን ፡ የሚገዛው ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
አእላፋት ፡ መላእክት ፡ ያከብሩታል ፡ ተመስገን ፡ እያሉ ፡ ይሰግዱለታል
  ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ኢየሱስን
  ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡

ዛሬ ፡ ነው ፡ የደስታ ፡ የምሥጋናችን ፡ ቀን
መርገምን ፡ አርቆዋል ፡ ሰርታል ፡ ስራችንን
በፍፁም ፡ ፈቃዱ ፡ እንዲሁ ፡ አድኖናል
ስገድትም ፡ ምሥጋናም ፡ ለእርሱ ፡ ያንስበታል
 ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ኢየሱስን
 ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡

አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ መጀመሪያው ፡ የሁሉ ፡ ፍጻሜ ፡ መጨረሻው
የሚመጣው ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የዓለምን ፡ ሃጥያት ፡ ያስወገደው
  ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ኢየሱስን
  ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡

ባባቱ ፡ ቀኝ ፡ ላለው ፡ ለጌታ ፡ ለኢየሱስ ፡
አምልኮ ፡ ዝማሬ ፡ ከልባችን ፡ ይፍሰስ
በክብር ፡ ታጅቦ ፡ በደመና ፡ ይመጣል ፡
ያለም ፡ ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ለክብሩ ፡ ይሰግዳል
  ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ኢየሱስን
  ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡

በዙፋኑ ፡ ላለው ፡ ክብር ፡ እንስጠው ፡ ይገባዋል ፡ ስግደት ፡ እናክብረው
በምሥጋና ፡ ዜማ ፡ በዕልልታ ፡ በፊቱ ፡ እንዘምር ፡ በደስታ
  ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ኢየሱስን
  ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡