ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ (Kante Lemar Eyesus) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(1)

ኢየሱስ ፡ ፍቅር
(Eyesus Feqer)

ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

ፍቅርን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ
ምህረትን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ ፡
ይቅርታን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ ፡
የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ
 የማይለወጥ ፡ የአንተ ፡ ፍቅር
 የማትሰለች ፡ ሁልጊዜ ፡ ምትምር
 ይቅርታህ ፡ ብዙ ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ
 ጌታ ፡ እንተን ፡ አየሁ ፡ በምድር ፡ በሰማይ

ትዕግሥትን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ
ቸርነት ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ
ማስተዋል ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ
የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ
 አየሁኝ ፡ ጌታ ፡ ስትታገሰኝ
 በቸርነትህ ፡ ስትለግሰኝ
 ታስደንቃለህ ፡ ማስተዋል ፡ አለህ
 ሚመስልህ ፡ የለም ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነህ

እውነትን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ
ዕውቀትን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ
ጥበብን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ
የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ
 አንተ ፡ እውነት ፡ ነህ ፡ እውነተኛ ፡ ነህ
 ሁሉን ፡ ፈጥረሃል ፡ ሁሉን ፡ ታውቃለህ
 ጥበበኛ ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ
 በምንም ፡ ነገር ፡ የማትረታ

የዋህነት ፡ ከአንተ ፡ ለማር ፡ ኢየሱስ
ትህትናን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ
መታዘዝ ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ
የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ
 አትጨክንም ፡ አንተ ፡ የዋህ ፡ ነህ
 ዝቅ ፡ ማለትን ፡ ታውቅበታለህ
 እስከሞት ፡ ድረስ ፡ አንተ ፡ ታዘዝህ
 ኢየሱስ ፡ ሙሉ ፡ ነህ ፡ ትማርካለህ