ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው (Eyesus Feqer New) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(1)

ኢየሱስ ፡ ፍቅር
(Eyesus Feqer)

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:07
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

ቀማኛ ፡ ረብሸኛ ፡ ሌባ ፡ ተንኮለኛ
ጨካኝ ፡ ነፍሰ ፡ ገዳይ ፡ እብሪተኛ ፡ ኃይለኛ
የፍቅር ፡ አባት ፡ ጋር ፡ ኢኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ሲደርስ
ልቡ ፡ ይማረካል ፡ ይረታል ፡ በኢየሱስ

ኢየሱስ ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል
ሌባውን ፡ ታማኝ ፡ ያደርጋል
ኢየሱስ ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል
ረብሸኛን ፡ ሰላማዊ ፡ ያደርጋል

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ያሸንፋል
በር ፡ ለከፈተለት ፡ ሁሉንም ፡ ይረታል
ኢየሱስ ፡ ያድሳል ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል
ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ድል ፡ ያደርጋል

ብዙ ፡ ተመሬያለሁ ፡ የሚለኝ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ
ዓለም ፡ ምን ፡ እንደሆን ፡ እኔ ፡ አውቃለሁኝ ፡ ባይ
የጥበብን ፡ መሰረት ፡ ጌታን ፡ ያገኝና
አምላኩን ፡ ይፈራል ፡ ዕውቀቱን ፡ ይረዳና

ኢየሱስ ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል
ትዕቢተኛን ፡ ትሁት ፡ ያደርጋል (፪x)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ያሸንፋል
በር ፡ ለከፈተለት ፡ ሁሉንም ፡ ይረታል
ኢየሱስ ፡ ያድሳል ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል
ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ይማርካል

ተስፋ ፡ የቆረጠው ፡ በሰው ፡ የተናቀው
ታናሽ ፡ የተባለው ፡ ዕውቀትም ፡ የሌለው
የዕውቀትን ፡ ሚስጥር ፡ ኢየሱስን ፡ አግኝቶ
ሩቁን ፡ ማየት ፡ ችላል ፡ ማስተዋል ፡ ተሞልቶ

ኢየሱስ ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል
የተናቀውን ፡ ከፍ ፡ ያደርጋል
ኢየሱስ ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል
የተናቀውን ፡ ያስከብራል

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ያሸንፋል
በር ፡ ለከፈተለት ፡ ሁሉንም ፡ ይረታል
ኢየሱስ ፡ ያድሳል ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል
ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ድል ፡ ያደርጋል

የጐደለኝ ፡ የለም ፡ ሰላማዊ ፡ ሰው ፡ ነኝ
ተኛለሁ ፡ እረፍት ፡ አለኝ ፡ ደህና ፡ አለኝ ፡ ደስታ ፡ አለኝ ፡
ሲል ፡ የኖረው ፡ ሀብታም ፡ ሲያደርግ ፡ እራሱን ፡ ደግ
ተረዳው ፡ በኢየሱስ ፡ መሆኑን ፡ የጠፋ ፡ በግ

ኢየሱስ ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል
ወደ ፡ ቤትም ፡ ያስገባል (፪x)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ያሸንፋል
በር ፡ ለከፈተለት ፡ ሁሉንም ፡ ይረታል
ኢየሱስ ፡ ያድሳል ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል
ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ድል ፡ ያደርጋል

ሸባው ፡ በአልጋ ፡ ወድቆ ፡ በበሽታ ፡ ማቆ
ቆሞ ፡ መሄድ ፡ ችሏል ፡ ኢየሱስን ፡ አውቆ
የሞተው ፡ ተንስቷል ፡ የእውሩም ፡ ዓይን ፡ በርቷል
እርሱ ፡ ሁሉን ፡ ይችላል ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል

ኢየሱስ ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል
ሽባውንም ፡ ያራምዳል
ኢየሱስ ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል
የሞተውን ፡ ያስነሳል

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ያሸንፋል
በር ፡ ለከፈተለት ፡ ሁሉንም ፡ ይረታል
ኢየሱስ ፡ ያድሳል ፡ ታሪክ ፡ ይለውጣል
ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ድል ፡ ያደርጋል (፪x)