እኔም ፡ ልወቅህ ፡ ዛሬ (Eniem Leweqeh Zarie) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(1)

ኢየሱስ ፡ ፍቅር
(Eyesus Feqer)

ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

ነፍሴ ፡ የአምላክሽን ፡ ክብር ፡ እይ ፡ ታላቅነቱ ፡ ይግባሽ
ጌታ ፡ መሆኑን ፡ ተረጂ ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ይሁን ፡ ልብሽ
ቸል ፡ አትበይ ፡ አትርሺ ፡ በዙፋኑ ፡ የተቀመጠውን
እንደሚገባሽ ፡ አክብሪው ፡ ማራኪሽ ፡ እርሱ ፡ ይሁን

እኔም ፡ ልወቅህ ፡ ዛሬ ፡ ልወቅህ ፡ እንደሚገባኝ
በፊትህ ፡ ልስገድልህ ፡ ክብርህን ፡ ጌታ ፡ አሳየኝ
ክብርህን ፡ አይቶ ፡ እንደነበረ ፡ የሚቀር ፡ ማን ፡ ነው
ብርሃንህን ፡ አይቶ ፡ የማይሰግድልህስ ፡ ማን ፡ ነው

ነፍሴ ፡ እርሱን ፡ ማየት ፡ ብትችይ ፡ ውበቱ ፡ ቢታይሽ
ከሁሉ ፡ የሚበልጥ ፡ መሆኑ ፡ ከልብስ ፡ ቢረዳሽ
ሰላምሽ ፡ ይበዛል ፡ ታርፊያልሽ ፡ ይቀራል ፡ ሁከትሽ
አምላክ ፡ እንደ ፡ አምላክነቱ ፡ ቢረዳሽ

ነፍሴ ፡ አምላክሽ ፡ ጠርቶሻል ፡ የልጁን ፡ ክብር ፡ እንድታይ
በምድር ፡ ኑሮ ፡ በሚፈርስ ፡ በድንክዋን ፡ ተይ ፡ አትታለይ
አምላክ ፡ ይረዳሻል ፡ መሻትሽ ፡ እሱን ፡ ብቻ ፡ ይሁን
ፈልጊው ፡ ተጠሚው ፡ ተራቢው ፡ ጌታሽን

ነፍሴ ፡ የእምነትን ፡ ብልጭታ ፡ አንጸባርቆልሻል
አምላክ ፡ እንድታውቂው ፡ እንድትቀርቢው ፡ ይሻል
አንድ ፡ ልጁን ፡ ልኮ ፡ እንዲሁ ፡ በፍቅሩ ፡ መርጦሻል
ነፍሴ ፡ እባክሽ ፡ ይግባሽ ፡ አክብሪው ፡ እርሱ ፡ ይበልጥብሻል

እዚህ ፡ ያደረሰሽ ፡ በስጋው ፡ መቼ ፡ ይለይሻል
ሃጢያተኛ ፡ ሳለሽ ፡ ሞቶልሽ ፡ በደሙ ፡ አጽድቆሻል
ከመልእክት ፡ በላይ ፡ አክብሮሽ ፡ በቀኙ ፡ አስቀምጦሻል
ነፍሴ ፡ እባክሽ ፡ ይግባሽ ፡ እርሱ ፡ አክብሮሻል