እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው (Egziabhier Denq New) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(1)

ኢየሱስ ፡ ፍቅር
(Eyesus Feqer)

ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

ከምናስበው ፡ ከምንገምተው ፡ ክምናውቀውም ፡ በላይ ፡ ነው
 እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ ድንቅ ፡ ነው

ማን ፡ ይመስለዋል ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
ሊቀረብ ፡ በማይቻል ፡ ብርሃን ፡ ውስጥ ፡ ነው
ከእርሱ ፡ በፊት ፡ አምላክ ፡ አልተሰራም ፡
ከእርሱ ፡ በሃላም ፡ ማንም ፡ ዓይኖርም
ከእግዚአብሔር ፡ ሌላ ፡ የሚያድን ፡ የለም

ባሕርን ፡ ከፍሎ ፡ መንገድ ፡ ያደርጋል
በምድረ ፡ በዳ ፡ ከአለት ፡ ውኃ ፡ ያፈልቃል
በደረቅ ፡ በርሃ ፡ መናን ፡ ይመግባል
ሸለቆውንም ፡ ውኃ ፡ ይሞላል
እርሱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ይችላል

ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ በቃሉ ፡ ፈጥራል
ከዋክብቶችን ፡ በስማቸው ፡ ይጥራል
የጸጉራችን ፡ ቁጥር ፡ በእርሱ ፡ ተቆጥራል
ልብን ፡ ኩላሊትን ፡ ይመረምራል
እግዚአብሔር ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ እርሱ ፡ ሁሉን ፡ ያውቃል

እግዚአብሔር ፡ ብቻውን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ነው
እንደርሱ ፡ ያለ ፡ የለም ፡ እግዚአብሔር ፡ ልዪ ፡ ነው ፡
ክሰው ፡ አእምሮ ፡ ከዕውቀቱ ፡ በላይ ፡ ነው
በምድር ፡ በሰማይ ፡ የተፈራ ፡ ነው
ከሁሉም ፡ ነገር ፡ በላይ ፡ ነው