ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታዬ (Des Yelegnal Begietayie) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(1)

ኢየሱስ ፡ ፍቅር
(Eyesus Feqer)

ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 6:54
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

አዝ፦ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በኢየሱሴ/በአምላኬ
ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታዬ
ሰላም ፡ ጤና ፡ ሆኗል ፡ ለኑሮዬ (፪x)

እወጣለሁ ፡ እገባለሁ ፡ እሰማራለሁ
የኢየሱስን ፡ ሰላም ፡ በሕይወቴ ፡ አያለሁ
በተከበበች ፡ ከተማ ፡ ምህረቱ ፡ ከቦኛል
በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ሰላም ፡ ሆኖልኛል

አዝ፦ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በኢየሱሴ/በአምላኬ
ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታዬ
ሰላም ፡ ጤና ፡ ሆኗል ፡ ለኑሮዬ (፪x)

ማህበሉ ፡ ቢነሳም ፡ እንኳን ፡ ወጀቡም ፡ ቢበዛ
ነፍሴ ፡ እረፍት ፡ አላት ፡ በኢየሱስ ፡ ተይዛ
በለስ ፡ ፍሬ ፡ ባታፈራ ፡ የወይራ ፡ ስራም ፡ ቢጐል
እኔ ፡ ግን ፡ በአምላኬ ፡ በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል

አዝ፦ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በኢየሱሴ/በአምላኬ
ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታዬ
ሰላም ፡ ጤና ፡ ሆኗል ፡ ለኑሮዬ (፪x)

የልቤ ፡ ጥያቄ ፡ ሞልቶ ፡ ሁሉ ፡ ቢሆንልኝ
ለእኔስ ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ አንድም ፡ አይሆንልኝ
የተሰወረውን ፡ ነገር ፡ የውስጥን ፡ ይረዳል
በእርሱ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ከሁሉም ፡ ይበልጣል

አዝ፦ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በኢየሱሴ/በአምላኬ
ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታዬ
ሰላም ፡ ጤና ፡ ሆኗል ፡ ለኑሮዬ (፪x)

ከታሰርኩበትም ፡ ፈቶ ፡ ነጻ ፡ አድርጐኛል
ውዴ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ከብሯል ፡ ከፍ ፡ ብላል
ኃጢአቴን ፡ አስወግዶልኝ ፡ ፅድቄ ፡ እርሱ ፡ ሆናል
በፊቱ ፡ ዘላለሁ ፡ በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል

አዝ፦ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በኢየሱሴ/በአምላኬ
ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታዬ
ሰላም ፡ ጤና ፡ ሆኗል ፡ ለኑሮዬ (፪x)

ኢየሱስ ፡ መልካም ፡ እረኛ ፡ ነው ፡ ነፍሴን ፡ መልሷታል
በፅድቅም ፡ መንገድ ፡ ወደ ፡ እውነት ፡ መርቷታል
በጌታዬ ፡ በኢየሱስ ፡ በእርሱ ፡ እመካለሁ
በእርሱ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ለእርሱ ፡ እገዛላሁ

አዝ፦ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በኢየሱሴ/በአምላኬ
ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታዬ
ሰላም ፡ ጤና ፡ ሆኗል ፡ ለኑሮዬ (፬x)