ብርሃን ፡ ነው ፡ ኢየሱስ (Berhan New Eyesus) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(1)

ኢየሱስ ፡ ፍቅር
(Eyesus Feqer)

ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

ብርሃን ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ብርሃን ፡ ነው
 ብርሃን ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ብርሃን ፡ ነው
 ጨለማን ፡ ያበራል ፡ ኢየሱስ ፡ ብርሃን ፡ ነው

በጨለማ ፡ ላለ ፡ ብርሃን ፡ ነው
ለተጨነቀ ፡ ሕዝብ ፡ መጽናናት ፡ ነው
ከሃጥያት ፡ የሚያድን ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
እውነትና ፡ መንገድ ፡ ሕይወትም ፡ ነው

ለተጠማ ፡ የሕይወት ፡ ውኃ ፡ ይሰጣል
በእርሱ ፡ የሚታመን ፡ መች ፡ ይራባል
ዘላለም ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ይኖራል
ባባቱ ፡ ቤት ፡ መሰማሪያ ፡ ያገኛል

በእርሱ ፡ የሚያምኑ ፡ ይድናሉ
ከሃጥያት ፡ በደሙ ፡ ይነጻሉ
የዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ይወርሳሉ
ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ አብረው ፡ ይከብራሉ

ኢየሱስ ፡ ቅርብ ፡ ነው ፡ ይገኛል
የሚፈልገው ፡ ልብ ፡ ደስ ፡ ይሰኛል
ሸክምን ፡ ያራግፋል ፡ እረፍት ፡ ያሰጣል
አእምሮና ፡ ልብን ፡ ያስርፋል