የሚመስልህ ፡ የለም (Yemimesleh Yelem) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(2)

እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ
(Egziabhieren Barki)

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:45
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

የሚመስልህ ፡ የለም ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ ፡
 የሚመስልህ ፡ የለም ፡ አንተ ፡ ድንቅ ፡ ነህ
 የሚመስልህ ፡ የለም ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ
 የሚመስልህ ፡ የለም ፡ አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ

ምህረትህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ከሕይወት ፡ ይሻላል
ፍቅርህም ፡ ጥልቅ ፡ ነው ፡ እንደሞት ፡ ይበረታል
ትዕግሥትህ ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ ዘመናት ፡ ያልፋል
እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፡ ማን ፡ ይመስልሃል

በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ በክብር ፡ ተቀምጠሃል
እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ነህ ፡ ብርሃንን ፡ ለበሰሃል
በቃልህ ፡ ሰማይን ፡ ምድር ፡ ፈጥረሃል
ኤልሻዳይ ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል

ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ ተመለከታለህ
ከቅዱስ ፡ ማደሪያ ፡ ትህዛዝ ፡ ትሰጣለህ
ፍጥረትን ፡ በሙሉ ፡ አንተ ፡ ትገዛላህ

ሰማይት ፡ ክብርህን ፡ ይናገራሉ
ፍጥረታት ፡ በሙሉ ፡ ድምጽህን ፡ ይሰማሉ ፡
ለቃልህ ፡ በፍርሃት ፡ ይታዘዛሉ
ክብርን ፡ በሙሉ ፡ ለአንተ ፡ ያመጣሉ

እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ የለም ፡ የሚመስልህ
እጅግ ፡ ከፍ ፡ ያልክ ፡ ነህ ፡ በግርማ ፡ ሞገስህ
ሰው ፡ በኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ አንተን ፡ ይቀርብሃል
በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ ደግሞ ፡ ይሰግድልሃል