ትሁቱ ፡ ከአንተ ፡ ልማር (Tehutu Kante lemar) - ነጻነት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ነጻነት ፡ አሰፋ
(Netsanet Assefa)

Lyrics.jpg


(2)

እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ
(Egziabhieren Barki)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 6:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የነጻነት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Netsanet Assefa)

እናንተ ፡ ፡ ደካሞች ፡ ሸክማችሁ ፡ የከበዳ ፡ ፡ ሁለ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ኑ ፡
እኔም ፡ አሳርፋችኋለሁ ፡ ቀንበሬን ፡ በላያችሁ ፡ ተሸከሙ ፡ ከእኔም ፡ ተማሩ
እኔ ፡ የዋህ ፡ በልቤም ፡ ትሁት ፡ ነኝና ፡ ለነፍሳችሁም ፡ እረፍት ፡ ታገኛላችሁ
ቀንበሬ ፡ ልዝብ ፡ ሸክሜም ፡ ቀሊል ፡ነውና ፡ (የማቲዎስ ፡ ወንጌል ፡ ምህራፍ ፡ ፲፩ ፡ ፳፮ ፴)

ያላሸከመከኝን ፡ እንዳልሸከም ፡
ከብዶኝ ፡ አንገዳግኝ ፡ እንዳልደክም
ያላሳየኸኝን ፡ አይቼ ፡
እንዳልቆም ፡ ግራ ፡ ተጋብቼ
ያልሰጠኸኝንም ፡ ወስጄ ፡
እንዳልቀር ፡ ኋላ ፡ ባዶ ፡ እጄን
የላደረከኝንም ፡ ሆኜ ፡
እንዳልቀል ፡ በአንተ ፡ ተመዝኜ
 ፡ ትሁቱ ፡ ከአንተ ፡ መማር ፡ እፈልጋለሁ
 ፡ ታዘኸውን ፡ እግዚአብሔርን ፡ ደስ ፡ እንዳስኘኸው
 ፡ ትሁቱ ፡ ከአንተ ፡ መማር ፡ እፈልጋለሁ
 ፡ ታዘኸውን ፡ እግዚአብሔርን ፡ ደስ ፡ እንዳስኘኸው
 ፡ አስተምረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ መንገድህን ፡
 ፡ አንተን ፡ ተክትዬ ፡ መራመድን
 ፡ እኔ ፡ ትሁት ፡ ነኝ ፡ ከኔ ፡ ተማሩ ፡ እንዳልክ
 ፡ እሺ ፡ አስተምረኝ ፡ አንተ ፡ እንደፈልክ

ስታዘኝ ፡ ሳልታዘዝህ ፡ ቀርቼ
እንዳልገኝ ፡ ለጠላቴ ፡ ተመችቼ
ስጠራኝ ፡ ድምጽህን ፡ ሳላውቀው ፡ ለይቼ
እንዳልጠፋ ፡ በክፉው ፡ እጅ ፡ ተነድቼ
ባስቀመጥከኝ ፡ በስፍራዬ ፡ ሳልቀመጥ
እንዳታጣኝ ፡ በቦታዬ ፡ ስትገለጥ
በሰጠኸኝ ፡ በመክሊቴ ፡ ሳላፈራ
እንዳትመጣብኝ ፡ የአንተን ፡ ስራ ፡ ሳልሰራ

በፈቃዴ ፡ በስሜቴ ፡ እየኖርኩኝ ፡
ጌታ ፡ እንዳልስት ፡ የአንተ ፡ ፈቃድ ፡ ነው ፡ እያልኩኝ
የቆምኩኝ ፡ መስሎኝ ፡ ሳልቆም ፡ የቀረሁ ፡ እንዳልሆን
እንዳልወድቅ ፡ ኋላ ፡ ልጠንቀቅ ፡ አሁን
አለሁ ፡ እያልኩኝ ፡ በቤትህም ፡ እኖራለሁ
ውጭ ፡ እንዳልሆን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እፈራለሁ ፡
ዛሬ ፡ ብገኝ ፡ በአንተ ፡ ወደ ፡ አምላክ ፡ ቀርቤ
እንዳልዘነጋው ፡ በአንተ ፡ መሆኑን ፡ መታሰቤ
 ፡ ትሁት ፡ የአንተን ፡ ቀንበር ፡ እሸከማለሁ
 ፡ ልዝብ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ማረስ ፡ እቻላለሁ
 ፡ ትሁት ፡ የአንተን ፡ ቀንበር ፡ እሸከማለሁ
 ፡ ልዝብ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ማረስ ፡ እቻላለሁ
 ፡ አንተን ፡ ተክትዬ ፡ መራመድን
 ፡ እኔ ፡ ትሁት ፡ ነኝ ፡ ከኔ ፡ ተማሩ ፡ እንዳልክ
 ፡ እሺ ፡ አስተመረኝ ፡ አንተ ፡ እንደፈልክ

አንተ ፡ ምራኝ ፡ አንተው ፡ መዳን ፡ እንደሆንከኝ
ፍጻሜዬን ፡ አንተው ፡ አሳምርልኝ
እንዳረከኝ ፡ ብቻ ፡ እንዳልከኝ ፡ አድርገኝ
ሁልጊዜ ፡ በአንተ ፡ ውስጥ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰውረኝ
አንተ ፡ እዘዘኝ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ በኔ ፡ ስራ
እኔም ፡ ከፈቃድህ ፡ ልስማማ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
ይስማማኛል ፡ ልዝብ ፡ ነው ፡ ቀንበርህ
አሸከመኝ ፡ ቀሊል ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ ሸክምህ
 ፡ ትሁቱ ፡ የአንተን ፡ ሸክም ፡ እሸከማለሁ
 ፡ ቀሊል ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ መሄን ፡ እችላለሁ
 ፡ ትሁት ፡ የአንተን ፡ ሸክም ፡ እሸከማለሁ
 ፡ ቀሊል ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ማሄድ ፡ እችላለሁ
 ፡ አስተምረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ መንገድህን ፡
 ፡ አንተን ፡ ተክትዬ ፡ መራመድን
 ፡ እኔ ፡ ትሁት ፡ ነኝ ፡ ከኔ ፡ ተማሩ ፡ እንዳልክ
 ፡ እሺ ፡ አስተመረኝ ፡ አንተ ፡ እንደፈልክ

አያስኬድም ፡ ሌላው ፡ ፈጽሞ ፡ አይመችም
የሚያስቆም ፡ ነው ፡ ወደፊት ፡ አያራምድም
አይስማማም ፡ ፍፁም ፡ አይሰጥም ፡ ደስታ
ባዶነት ፡ ነው ፡ ከንቱ ፡ ያለ ፡ አንተ ፡ ጌታ
ማትረፍ ፡ የለም ፡ መክሰር ፡ ነው ፡ በጉዞዬ
የለአንተ ፡ ግቡ ፡ አይደርሥም ፡ አላማዬ ፡
እንተ ፡ እንዳልክ ፡ ከአንተ ፡ መማርን ፡ መርጣለሁ
ስታደርገው ፡ እያየሁ ፡ አከብርሃለሁ
 ፡ ትሁቱ ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ እሺ ፡ እላላሁ
 ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ አርፌ ፡ መጉዋዝን ፡ እሻለሁ
 ፡ ትሁቱ ፡ የአንተን ፡ ቀንበር ፡ እሸከማለሁ
 ፡ ልዝህብ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ማረስ ፡ እችላለሁ
 ፡ ትሁቱ ፡ የአንተን ፡ ሸክም ፡ እሸከማለሁ
 ፡ ቀሊል ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ መሄድ ፡ እችላለሁ